ወደ ንጉሡም ቀርበው ስለ ንጉሡ ትእዛዝ፥ “ንጉሥ ሆይ! ከአንተ በቀር እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ከአምላክ ወይም ከሰው የሚለምን ሰው ሁሉ በአንበሶች ጕድጓድ ውስጥ እንዲጣል ትእዛዝ አልጻፍህምን?” አሉት። ንጉሡም መልሶ፥ “ነገሩ እንደማይለወጠው እንደ ሜዶንና እንደ ፋርስ ሕግ እውነት ነው” አላቸው።