ያን ጊዜም በኢየሩሳሌም ከነበረው ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የመጡትን የወርቁንና የብሩን ዕቃዎች አመጡ፤ ንጉሡና መኳንንቱም፥ ሚስቶቹና ቁባቶቹም ጠጡባቸው።