La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 6:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በተ​ማ​ረ​ኩ​ባ​ትም ሀገር ሆነው በል​ባ​ቸው ንስሓ ቢገቡ፥ በም​ር​ኮ​አ​ቸ​ውም ሀገር ሳሉ ተመ​ል​ሰው፦ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ናል፥ በድ​ለ​ን​ማል፥ ክፉም አድ​ር​ገ​ናል ብለው ቢለ​ም​ኑህ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በተጋዙበት አገር ሳሉ ወደ ልቡናቸው ቢመለሱ፣ ንስሓ ቢገቡና በምርኮ ሳሉ፣ ‘ኀጢአት ሠርተናል፤ በድለናል፤ ክፉ ድርጊትም ፈጽመናል’ ብለው ቢለምኑህ፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በተማረኩበትም አገር ሆነው በልባቸው ንስሐ ቢገቡ፥ በምርኮአቸውም አገር ሳሉ ተመልሰው፦ ‘ኃጢአት ሠርተናል፥ ስሕተት ፈጽመናል፥ ክፉም አድርገናል’ ብለው ቢለምኑህ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ምርኮኞች ሆነው በሚኖሩበት በዚያች አገር ሳሉ ‘ኃጢአት ሠርተናል፤ በድለናል፤ ዐምፀናልም’ ብለው በመናዘዝ ተጸጽተው ንስሓ ቢገቡ እግዚአብሔር ሆይ፥ ጸሎታቸውን ስማ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በተማረኩበትም አገር ሆነው በልባቸው ንስሐ ቢገቡ፥ በምርኮአቸውም አገር ሳሉ ተመልሰው ‘ኀጢአት ሠርተናል፤ በድለንማል፤ ክፉም አድርገናል፤’ ብለው ቢለምኑህ፥

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 6:37
17 Referencias Cruzadas  

“የማ​ይ​በ​ድል ሰው የለ​ምና አን​ተን ቢበ​ድሉ፥ ብት​ቈ​ጣ​ቸ​ውም፥ ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አሳ​ል​ፈህ ብት​ሰ​ጣ​ቸው፥ ሩቅም ወይም ቅርብ ወደ ሆነ ሀገር ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው ቢማ​ር​ኩ​አ​ቸው፥


በተ​ማ​ረ​ኩ​በ​ትም ሀገር ሳሉ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውና በፍ​ጹም ነፍ​ሳ​ቸው ወደ አንተ ቢመ​ለሱ፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ሰጠ​ሃት ወደ ምድ​ራ​ቸው፥ ወደ መረ​ጥ​ሃ​ትም ከተማ፥ ለስ​ም​ህም ወደ ሠራ​ሁት ቤት ቢጸ​ልዩ፥


በስሜ የተ​ጠ​ሩት ሕዝቤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አዋ​ር​ደው ቢጸ​ልዩ፥ ፊቴ​ንም ቢፈ​ልጉ፥ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም ቢመ​ለሱ፥ በሰ​ማይ ሆኜ እሰ​ማ​ለሁ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር እላ​ለሁ፤ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም እፈ​ው​ሳ​ለሁ።


እኔ ባሪ​ያህ ዛሬ በፊ​ትህ ስለ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሌሊ​ትና ቀን የም​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮ​ዎ​ችህ ያድ​ምጡ፤ ዐይ​ኖ​ች​ህም ይከ​ፈቱ፤ በአ​ንተ ላይም ያደ​ረ​ግ​ነ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ኀጢ​አት ለአ​ንተ እን​ና​ዘ​ዛ​ለን፤ እኔም፥ የአ​ባ​ቴም ቤት በድ​ለ​ናል።


በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው፤