የቀሩትም የፊተኞቹና የኋለኞቹ የአሜስያስ ነገሮች፥ እነሆ፥ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
2 ዜና መዋዕል 36:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀሩትም የኢዮአቄም ነገሮች፥ ያደረገውም ርኵሰት፥ በእርሱም የተገኘው ሁሉ፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል፤ ኢዮአቄምም እንደ አባቶቹ አንቀላፋ፤ ከአባቶቹም ጋር በጋኖዛን ከተማ ተቀበረ። ልጁም ኢኮንያን ከእርሱ ቀጥሎ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባሩ የፈጸመው አስጸያፊ ድርጊትና በርሱ ላይ የተገኘበት ነገር ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል። ልጁ ዮአኪንም በምትኩ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀረውም የኢዮአቄም ነገር፥ ያደረገውም ርኩሰት፥ በእርሱም የተገኘው ሁሉ፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል፤ ልጁም ዮአኪን በእርሱ ፋንታ ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ኢዮአቄም ያደረገው ሁሉ፥ አጸያፊ የሆነው ልማዱና የፈጸመው ክፉ ነገር ጭምር፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጻሕፍት ተመዝግቦ ይገኛል፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢኮንያን ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀረውም የኢዮአቄም ነገር፥ ያደረገውም ርኵሰት፥ በእርሱም የተገኘው ሁሉ፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል፤ ልጁም ዮአኪን በእርሱ ፋንታ ነገሠ። |
የቀሩትም የፊተኞቹና የኋለኞቹ የአሜስያስ ነገሮች፥ እነሆ፥ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
“እኔ ሕያው ነኝ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን ሆይ፥ አንተን በሰወርሁበት ቀኝ እጄ እንዳለ ማሕተም ነበርህ፤ እንግዲህ ወዲህ ግን እንደማትኖር እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል እግዚአብሔር፤
ኢኮንያን ተዋረደ፤ ለምንም እንደማይጠቅም የሸክላ ዕቃ ሆነ፤ እርሱንና ዘሩን ወደማያውቀው ሀገር ወርውረው ጥለውታልና።