La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 36:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የተ​ረ​ፉ​ት​ንም ወደ ባቢ​ሎን ማረ​ካ​ቸው፤ የሜ​ዶ​ንም ንጉሥ እስ​ኪ​ነ​ግሥ ድረስ ለን​ጉ​ሡና ለል​ጆቹ ባሪ​ያ​ዎች ሆኑ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከሰይፍ የተረፉትን ቅሬታዎች በምርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤ እስከ ፋርስ መንግሥት መነሣትም ድረስ የእርሱና የልጆቹ አገልጋዮች ሆኑ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከሰይፍም ያመለጡትን ወደ ባቢሎን ማረካቸው፤ የፋርስ ንጉሥም እስኪነግሥ ድረስ ለንጉሡና ለልጆቹ ባርያዎች ሆኑ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሰይፍ ከመገደል የተረፉትንም ሁሉ ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤ እነርሱም የፋርስ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት እስከ ተነሣበት ጊዜ ድረስ፥ በዚያው በባቢሎን ባሪያዎች ሆነው፥ ንጉሥ ናቡከደነፆርንና የእርሱን ዘሮች ያገለግሉ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከሰይፍም ያመለጡትን ወደ ባቢሎን ማረካቸው፤ የፋርስ ንጉሥም እስኪነግሥ ድረስ ለንጉሡና ለልጆቹ ባሪያዎች ሆኑ፤

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 36:20
13 Referencias Cruzadas  

የአ​በ​ዛ​ዎች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ የቀ​ረ​ውን ሕዝብ፥ ሸሽ​ተ​ውም ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ የተ​ጠ​ጉ​ትን፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወሰደ።


በኤ​ር​ም​ያ​ስም አፍ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ በፋ​ርስ ንጉሥ በቂ​ሮስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፋ​ር​ስን ንጉሥ የቂ​ሮ​ስን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ በመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ሁሉ አዋጅ ይነ​ገር ዘንድ በጽ​ሕ​ፈት እን​ዲህ ሲል አዘዘ፤


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ ባቢ​ሎን ከማ​ረ​ካ​ቸው ምር​ኮ​ኞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየ​ከ​ተ​ማ​ቸው የተ​መ​ለ​ሱት የሀ​ገር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።


አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የሰ​ማ​ይን አም​ላክ ከአ​ስ​ቈጡ በኋላ በከ​ለ​ዳ​ዊው በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ይህን ቤት አፈ​ረሰ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ባቢ​ሎን አፈ​ለሰ።


በሕ​ዝቤ ላይ ተቈ​ጥቼ ነበር፤ ርስ​ቴ​ንም አረ​ከ​ስሽ፤ በእ​ጅ​ሽም አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸው አል​ራ​ራ​ሽም፤ ቀን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም እጅግ አክ​ብ​ደ​ሻል።


ይህ​ችም ምድር ሁሉ ትጠ​ፋ​ለች፤ ለእ​ነ​ዚ​ህም አሕ​ዛ​ብና ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሰባ ዓመት ይገ​ዛሉ።


የገዛ ራሱም ምድር ጊዜ እስ​ኪ​መጣ ድረስ አሕ​ዛብ ሁሉ ለእ​ር​ሱና ለልጁ ለልጅ ልጁም ይገ​ዛሉ፤ በዚ​ያን ጊዜም ብዙ አሕ​ዛ​ብና ታላ​ላ​ቆች ነገ​ሥ​ታት ለእ​ርሱ ይገ​ዙ​ለ​ታል።


ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር የማ​ረ​ከው ሕዝብ ይህ ነው፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ሦስት ሺህ ሃያ ሦስት አይ​ሁድ፤


አሁ​ንም በም​ድረ በዳ፥ በደ​ረ​ቅና በተ​ጠ​ማች መሬት ተተ​ከ​ለች።


ፋር​ስ​ንና ኢት​ዮ​ጵ​ያን፥ ሊብ​ያ​ንም፥ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ጋሻና የራስ ቍርን የለ​በ​ሱ​ትን ሁሉ፥


የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጠሽ ውለጂ፥ አሁን ከከተማ ትወጫለሽና፥ በሜዳም ትቀመጫለሽ፥ ወደ ባቢሎንም ትደርሻለሽ፥ በዚያም ያድንሻል፥ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።