2 ዜና መዋዕል 35:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስራኤልም ሁሉ መሥራት የሚችሉትን ሌዋውያን ራሳቸውን ለእግዚአብሔር እንዲያነጹና ቅድስቲቱንም ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ እንዲያኖሩ አዘዛቸው። ንጉሡም ኢዮስያስ አለ፥ “በትከሻችሁ የምትሸከሙት አንዳች ነገር አይኑር፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልን ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩትና ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አላቸው፤ “የእግዚአብሔርን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ባሠራው ቤተ መቅደስ አኑሩ፤ በእናንተ ትከሻ አትሸከሙት፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለጌታም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ፦ “ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም፤ አሁንም አምላካችሁን ጌታንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለለዩ፥ የመላው እስራኤል መምህራን ለሆኑ ሌዋውያን እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጠ፦ “የተቀደሰውን የቃል ኪዳን ታቦት የዳዊት ልጅ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ባሠራው ቤተ መቅደስ ውስጥ አኑሩት፤ ከእንግዲህ ወዲህ እናንተ አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን ማገልገል እንጂ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት በትከሻችሁ ተሸክማችሁ ከስፍራ ወደ ስፍራ መውሰድ የለባችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለእግዚአብሔርም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ “ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ፤ |
በነገሠም በሦስተኛው ዓመት በይሁዳ ከተሞች ያስተምሩ ዘንድ መሳፍንቱንና ኀያላኑን ሰዎች አብድያስን፥ ዘካርያስን፥ ናትናኤልን፥ ሚኪያስን ላከ።
ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር አገልግሎት አስተዋዮች የነበሩትን ሌዋውያንን ሁሉ ያጽናና ነበር። የደኅንነትም መሥዋዕት እያቀረቡ፥ የአባቶቻቸውንም አምላክ እያመሰገኑ ሰባት ቀን በዓል አደረጉ።
ወደ እግዚአብሔርም ቤት የቀረበውን ገንዘብ ባመጡ ጊዜ ካህኑ ኬልቅያስ በሙሴ እጅ የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ አገኘ።
ካህናቱም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤትዋ አምጥተው በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ከኪሩቤል ክንፍ በታች በነበረው መቅደስ አኖሯት።
ሰሎሞንም፥ “የእግዚአብሔር ታቦት የገባችበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት አትቀመጥም” ሲል የፈርዖንን ልጅ ከዳዊት ከተማ ወደ ሠራላት ቤት አወጣት።
ሙሴም፥ “ዛሬ በረከትን እንዲያወርድላችሁ ከእናንተ እያንዳንዱ ከልጁና፥ ከወንድሙ የተነሣ እግዚአብሔርን በእጃችሁ ደስ አሰኛችሁት” አላቸው።
ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።
ሌዋውያንንም ስጦታ አድርጌ አገባኋቸው፤ ልዩ በሆነች ድንኳን ውስጥ የእስራኤልን ልጆች ሥራ ይሠሩ ዘንድ፥ የእስራኤልንም ልጆች ኀጢአት ያቃልሉ ዘንድ ከእስራኤል ልጆች መካከል ለአሮንና ለልጆቹ ተሰጡ፤ ከእስራኤልም ልጆች ወደ መቅደስ የሚቀርብ አይኑር።”
ኢየሱስ ክርስቶስን ጌታ እንደ ሆነ እንሰብካለን እንጂ ራሳችንን የምንሰብክ አይደለም፤ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም ብለን ራሳችንን ለእናንተ አስገዛን።
ፍርድህን ለያዕቆብ፥ ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ፤ በማዕጠንትህ ዕጣንን፥ በመሠዊያህም የሚቃጠል መሥዋዕትን ሁልጊዜ ያቀርባሉ።