እግዚአብሔርም፦ በምን ታስተዋለህ? አለው፤ እርሱም ወጥቼ በነቢያቱ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ። እግዚአብሔርም፦ ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፤ ይሆንልሃልም፤ ውጣ፤ እንዲሁም አድርግ አለ።
2 ዜና መዋዕል 32:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ሕዝቅያስ አያስታችሁ፤ በእነዚህም ቃላት እንድትተማመኑ አያድርጋችሁ፤ አትመኑትም፤ ከአሕዛብና ከመንግሥታት አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄና ከአባቶች እጅ ያድን ዘንድ ማንም አልቻለም፤ ስለዚህም አምላካችሁ ከእጄ ያድናችሁ ዘንድ አይችልም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ሕዝቅያስ አያታልላችሁ፤ አያስታችሁም። የየትኛውም አገር ሕዝብ ወይም መንግሥት አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ወይም ከአባቶቼ እጅ መታደግ የቻለ ስለሌለ አትመኑት። የእናንተ አምላክማ ከእጄ ያድናችሁ ዘንድ ምንኛ ያንስ!” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ሕዝቅያስ አያስታችሁ፥ እንዲህም አያባብላችሁ፥ አትመኑትም፤ ከአሕዛብና ከመንግሥታት አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄና ከአባቶቼ እጅ ለማዳን ማንም አልቻለም፤ ይልቁንስ አምላካችሁ ከእጄ ሊያድናቸሁ እንዴት ይችላል?’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሕዝቅያስ በዚህ መንገድ አያታላችሁ! ወደ ስሕተትም አይምራችሁ! ከቶ እርሱን አትመኑ! የማንም ሕዝብ አምላክ የራሱን ሕዝብ ከማንኛውም የአሦር ንጉሠ ነገሥት እጅ ሊያድን የቻለበት ጊዜ የለም፤ ይህም የእናንተ አምላክ እናንተን ሊያድን እንደማይችል የተረጋገጠ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ሕዝቅያስ አያስታችሁ፤ እንዲህም አያባብላችሁ፤ አትመኑትም፤ ከአሕዛብና ከመንግስታት አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄና ከአባቶቼ እጅ ያድን ዘንድ ማንም አልቻለም፤ ይልቁንስ አምላካችሁ ከእጄ ያድናችሁ ዘንድ እንዴት ይችላል?’” |
እግዚአብሔርም፦ በምን ታስተዋለህ? አለው፤ እርሱም ወጥቼ በነቢያቱ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ። እግዚአብሔርም፦ ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፤ ይሆንልሃልም፤ ውጣ፤ እንዲሁም አድርግ አለ።
“ለይሁዳ ንጉሥ ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም ብሎ የምትታመንበት አምላክህ አያታልልህ።
አምላካችን እግዚአብሔር ከአሦር ንጉሥ እጅ ያድነናል እያለ ለራብ፥ ለጥምና ለሞት አሳልፎ ይሰጣችሁ ዘንድ የሚያሳስታችሁ ሕዝቅያስ አይደለምን?
ፈርዖንም አላቸው፥ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፤ እነሆ፥ እናንተን ስለቅ ልጆቻችሁንም መልቀቅ አለብኝን? ክፉ ነገር እንደሚገጥማችሁ ዕወቁ።
ፈርዖንም፥ “የእስራኤልን ልጆች እለቅቅ ዘንድ ቃሉን የምሰማው እርሱ እግዚአብሔር ማን ነው? እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም ደግሞ አልለቅቅም” አለ።
ሕዝቅያስም፦ እግዚአብሔር ያድነናል ብሎ አያታልላችሁ። በውኑ የአሕዛብ አማልክት ሀገሮቻቸውን ከአሦር ንጉሥ እጅ አድነዋቸዋልን?
አሁን ግን እንደምታዩትና እንደምትሰሙት ይህ ጳውሎስ ኤፌሶንን ብቻ ሳይሆን መላውን እስያን አሳተ፤ ብዙ ሕዝብንም መለሰ፤ በሰው እጅ የሚሠሩትንም ሁሉ አማልክት አይደሉም አላቸው።
አሁንስ ለእግዚአብሔር ያይደለ ለሰው ብዬ አስተምራለሁን? ወይስ ሰውን ደስ አሰኛለሁን? ሰውን ደስ ላሰኝ ብወድስ የክርስቶስ ባሪያ አይደለሁም።