2 ዜና መዋዕል 31:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በይሁዳም ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤልና የይሁዳ ልጆች የበሬዉንና የበጉን፥ የፍየሉንም ዐሥራት አመጡ፤ ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርም ቀደሱት፤ ከምረውም አኖሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በይሁዳ ከተሞች ይኖሩ የነበሩት የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎችም ከከብቶቻቸው፣ ከበግና ከፍየል መንጎቻቸውና ለአምላካቸው እግዚአብሔር ከለዩአቸው የተቀደሱ ነገሮች ዐሥራት አውጥተው አመጡ፤ ከመሩትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በይሁዳም ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤልና የይሁዳም ልጆች የበሬውንና የበጉን አሥራት፥ ለአምላካቸውም ለጌታ የተቀደሰውን አሥራት አመጡ፥ ከምረውም አስቀመጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በይሁዳ ከተሞች ሰዎችም ሕዝብም ሁሉ ከቀንድ ከብቶቻቸውና ከበጎቻቸው ዐሥራት አውጥተው ሰጡ፤ እንዲሁም ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር የተለየ ያደረጉትን ስጦታ አምጥተው ከመሩት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በይሁዳም ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤልና የይሁዳም ልጆች የበሬውንና የበጉን አሥራት፥ ለአምላካቸውም ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን አሥራት አመጡ፤ ከምረውም አኖሩት። |
“የምድርም ዐሥራት፥ ወይም የምድር ዘር፥ ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ነው፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።