የይሁዳም ሕዝብ በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለቀዳምያት፥ ለዐሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎችን ሾሙ።
2 ዜና መዋዕል 31:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ነገር እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች የእህሉንና የወይኑን፥ የዘይቱንና የማሩንም፥ የእርሻውንም ፍሬ መጀመሪያ ሁሉ ሰጡ፤ የሁሉንም ዐሥራት አብዝተው አቀረቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትእዛዙ እንደ ወጣ እስራኤላውያን ወዲያውኑ የእህሉንና የአዲሱን ወይን ጠጅ፣ የዘይቱንና የማሩን እንዲሁም የዕርሻውን ፍሬ ሁሉ በኵራት በልግስና ሰጡ፤ ካላቸው ከማንኛውም ነገር ሁሉ ላይ እጅግ ብዙ የሆነ ዐሥራት አውጥተው አመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንም ነገር እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች የእህሉንና የወይኑን ጠጅ የዘይቱንና የማሩንም፥ የእርሻውንም ፍሬ ሁሉ በብዛት ሰጡ፤ የሁሉንም አሥራት በብዛት አቀረቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ይህን የንጉሡን ትእዛዝ እንደ ሰሙ ከእህላቸውና ከወይን ጠጃቸው፥ ከወይራ ዘይታቸውና ከማራቸው ከሌላውም የእርሻቸው ፍሬ ሁሉ ምርጥ የሆነውን በኲራት በልግሥና አበረከቱ፤ ከነበራቸውም ሀብት ሁሉ ዐሥራት አውጥተው ሰጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ነገር እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች የእህሉንና የወይኑን ጠጅ የዘይቱንና የማሩንም፥ የእርሻውንም ፍሬ ሁሉ በኵራት ሰጡ፤ የሁሉንም አሥራት አብዝተው አቀረቡ። |
የይሁዳም ሕዝብ በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለቀዳምያት፥ ለዐሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎችን ሾሙ።
በየጊዜውም ዕንጨት ለሚሸከሙ ሰዎች ቍርባን፥ ለበኵራቱም ሥርዐት አደረግሁ። “አምላካችን ሆይ፥ በመልካም አስበኝ።”
የሰባቱንም ሱባዔ በዓል ታደርጋለህ፤ እርሱም የስንዴ መከር መጀመሪያ ነው፤ በዓመቱም መካከል የመክተቻ በዓል ታደርጋለህ።
የመጀመሪያውን የምድርህን ፍሬ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወስዳለህ። ጠቦቱን በእናቱ ወተት አትቀቅል።”
ከእናንተ ዘንድ ለእግዚአብሔር ቍርባንን አቅርቡ፤ የልብ ፈቃድ ያለው ከገንዘቡ የመጀመሪያውን ለእግዚአብሔር ያምጣ፤ ወርቅና ብር፥ ናስም፤
“የምድርም ዐሥራት፥ ወይም የምድር ዘር፥ ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ነው፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።
ለእግዚአብሔር ከሚሰጡት የፍሬ መጀመሪያ ከዘይትና ከወይን ከስንዴም የተመረጠውን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ፤
ወደ እግዚአብሔር የሚያመጡት በምድራቸው ያለው የፍሬ መጀመሪያ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው፤
እግዚአብሔርም አሮንን ተናገረው፤ እንዲህም አለው፥ “እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ለእኔ የለዩትን የመጀመሪያውን ቍርባኔን ሁሉ ትጠብቁ ዘንድ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ፤ ለአንተ እስክታረጅ፥ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ የዘለዓለም ሕግ እንዲሆን ሰጥቼሃለሁ።
ነገር ግን የሚተክዝ ዓለም ብቻ አይደለም፤ የመንፈስ ቅዱስን ፈለማ የተቀበልነው እናም ደግሞ እናዝናለን እንጂ፤ የነፍሳችንን ድኅነት እናገኝ ዘንድ የልጅነትን ክብር ተስፋ እናደርጋለንና፤ በእምነትም ድነናልና።
ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።