2 ዜና መዋዕል 31:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሳዶቅም ወገን የሆነ ታላቁ ካህን ዓዛርያስ፥ “ሕዝቡ መባውን ወደ እግዚአብሔር ፊት ማቅረብ ከጀመረ ወዲህ በልተናል፤ ጠጥተናልም፤ ጠግበናልም፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን ባርኮአልና ብዙ ተርፎአል፤ ከዚህም ገና ብዙ ተረፈ” ብሎ ተናገረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሳዶቅ ቤተ ሰብ የሆነው ሊቀ ካህናቱ ዓዛርያስም፣ “ሕዝቡ ስጦታውን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ማምጣት ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ፣ በቂ ምግብ አግኝተናል፤ ብዙም ተርፎናል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለባረከም ይህን ያህል ብዛት ያለው ሊተርፍ ችሏል” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሳዶቅም ወገን የሆነ ታላቁ ካህን ዓዛርያስ፦ “ሕዝቡ ቁርባኑን ወደ ጌታ ቤት ማቅረብ ከጀመረ ወዲህ በልተናል፥ ጠግበናልም፥ ጌታ ሕዝቡን ባርኮአልና ብዙ ተርፎአል፤ የተረፈውም ይህ ክምር ትልቅ ነው” ብሎ ተናገረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሳዶቅ ዘር የሆነው ሊቀ ካህናት ዐዛርያስም ንጉሡን፥ “ሕዝቡ ዐሥራቱን ወደ እግዚአብሔር ቤት ማምጣት ከጀመረ ወዲህ፥ እነሆ፥ በቂ ምግብ አለን፤ ብዙም ተርፎናል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለ ባረከ እነሆ፥ ይህን ሁሉ በብዛት አግኝተናል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሳዶቅም ወገን የሆነ ዋነኛው ካህን ዓዛርያስ “ሕዝቡ ቍርባኑን ወደ እግዚአብሔር ቤት ማቅረብ ከጀመረ ወዲህ በልተናል፤ ጠግበናል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ባርኮአልና ብዙ ተርፎአል፤ የተረፈውም ይህ ክምር ትልቅ ነው” ብሎ ተናገረ። |
የግዞት ቤቱ ጠባቂዎች አለቃም በግዞት ቤት የሚደረገውን ሁሉ ምንም አያውቅም ነበር፤ ሁሉን ለዮሴፍ ትቶለት ነበር፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረና፤ የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ ያቀናለት ነበር።
እንዲህም ሆነ፤ በቤቱ ባለውም ሁሉ ላይ ከሾመው በኋላ እግዚአብሔር የግብፃዊውን ቤት በዮሴፍ ምክንያት ባረከው። የእግዚአብሔርም በረከት በቤቱም፥ በእርሻውም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ።
ንጉሡም በእርሱ ፋንታ የዮዳሄን ልጅ በንያስን የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመ፤ መንግሥቱም በኢየሩሳሌም ጸናች። በአብያታርም ፋንታ ካህኑን ሳዶቅን ሾመ።
አቤቱ አምላካችን ሆይ፥ ለቅዱስ ስምህ ቤት እሠራ ዘንድ ይህ ያዘጋጀሁት ባለጠግነት ሁሉ ከእጅህ የመጣ ነው፤ ሁሉም የአንተ ነው።
ንጉሡም ሕዝቅያስና የእግዚአብሔር ቤት አለቃ ዓዛርያስ እንደ አዘዙ ኢዮኤል፥ ዓዛዝያ፥ አናኤት፥ ኡሳሄል፥ ኢያሪሞት፥ ኢዮዛብድ፥ ኤልሄል፥ ሰማኪያ፥ መሐት፥ በናያስና ልጆቹ፥ ከኮክንያስና ከወንድሙ ከሰሜኢ እጅ በታች ተቈጣጣሪዎች ነበሩ።
“ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ከእኔ ዘንድ በሳቱ ጊዜ የመቅደሴን ሥርዐት የጠበቁ የሳዶቅ ልጆች ሌዋውያን ካህናት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀርባሉ፤ ስቡንና ደሙንም ወደ እኔ ያቀርቡ ዘንድ በፊቴ ይቆማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
የበኵራቱ ሁሉ መጀመሪያ ከየዓይነቱ፥ ከቍርባናችሁም ሁሉ የማንሣት ቍርባን ሁሉ ለካህናት ይሆናል፤ በቤታችሁም ውስጥ በረከት ያድር ዘንድ የአዝመራችሁን ቀዳምያት ለካህናቱ ትሰጣላችሁ።
ከዛሬው ከዘጠነኛው ወር ከሀያ አራተኛው ቀን ጀምራችሁ የሚመጣውን ዘመን ልብ አድርጉ፣ የእግዚአብሔር መቅደስ መሠረት ከተተከለበት ቀን ጀምሮ ልብ አድርጉ።
በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር በረከቱን በአንተ ላይ፥ በጎተራህ፥ በእህልህም ሥራ ሁሉ እንዲወርድ ይልካል፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ይባርክሃል።
ነገር ግን ሁሉ አለኝ፤ ይበዛልኝማል፤ የመዓዛ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን፥ ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከአፍሮዲጡ ተቀብዬ አሟልቻለሁ።
ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።