እግዚአብሔርም ታላላቅ አንበሪዎችን፥ ውኃ ያስገኘውን ተንቀሳቃሽ ሕያው ፍጥረትን ሁሉ በየወገኑ፥ የሚበርሩ አዕዋፍንም ሁሉ በየወገናቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
2 ዜና መዋዕል 30:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቅያስም ስለ እነርሱ እንዲህ ሲል ጸለየ፥ “ምንም እንደ መቅደሱ ማንጻት ባይነጻ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልቡን የሚያቀናውን ሁሉ ቸሩ እግዚአብሔር ይቅር ይበለው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንም እንኳ በመቅደሱ ሥርዐት መሠረት የነጹ ሆነው ባይገኙም፣ የአባቶቻቸው አምላክ የሆነውን እግዚአብሔር አምላካቸውን ለመፈለግ ልባቸውን የሚያዘጋጁትን ሁሉ ይቅር በላቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ መቅደሱ የማንጻት ሥርዓት ሳይሆን የአባቶቹን አምላክ ጌታን ለመፈለግ ልቡን አቅንቶአልና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን በሥርዓት ያላነጹ ቢሆኑም እንኳ እነሆ በፍጹም ልባቸው አንተን በማምለክ ላይ ይገኛሉ፤ ስለዚህ በቸርነትህ ይቅር በላቸው!” ሲል ጸለየ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቅያስም “ምንም እንደ መቅደሱ ማንጻት ባይነጻ የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልቡን የሚያቀናውን ሁሉ ቸሩ እግዚአብሔር ይቅር ይበለው” ብሎ ስለ እነርሱ ጸለየ። |
እግዚአብሔርም ታላላቅ አንበሪዎችን፥ ውኃ ያስገኘውን ተንቀሳቃሽ ሕያው ፍጥረትን ሁሉ በየወገኑ፥ የሚበርሩ አዕዋፍንም ሁሉ በየወገናቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
አቤቱ፥ የአባቶቻችን የአብርሃምና የይስሐቅ የእስራኤልም አምላክ ሆይ፥ ይህን አሳብ በሕዝብህ ልብ ላይ ለዘለዓለም ጠብቅ፤ ልባቸውንም ወደ አንተ አቅና።
ነገር ግን የማምለኪያ ዐፀዶችን ከምድረ ይሁዳ አስወግደሃልና፥ እግዚአብሔርንም ትፈልግ ዘንድ ልብህን አዘጋጅተሃልና መልካም ነገር ተገኝቶብሃል” አለው።
ነገር ግን ኮረብታዎች ገና በዚያ ነበሩ፤ ሕዝቡም ገና ልባቸውን ወደ አባቶቻቸው አምላክ ወደ እግዚአብሔር አላቀኑም ነበር።
ከምርኮም ተመልሰው የመጡት የእስራኤል ልጆች፥ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ ራሳቸውን ከምድር አሕዛብ ርኵሰት ለይተው ወደ እነርሱ መጥተው የነበሩት ሁሉ ፋሲካውን በሉ፤
ዕዝራም የእግዚአብሔርን ሕግ ይፈልግና ያደርግ ዘንድ፥ ለእስራኤልም ሥርዐትንና ፍርድን ያስተምር ዘንድ ልቡን አዘጋጅቶ ነበር።
ከደምዋም እስክትነጻ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቈይ፤ የመንጻቷ ቀንም እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰን ነገር አትንካ፤ ወደ መቅደስም አትግባ።
ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ፥ “በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና ምስሎቻቸውን ከመካከላችሁ አርቁ፤ ልባችሁንም ወደ እግዚአብሔር አቅኑ፤ እርሱንም ብቻ አምልኩ፤ እርሱም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድናችኋል” ብሎ ተናገራቸው።