እንደዚህም ያለ ፋሲካ በእስራኤል ላይ ይፈርዱ ከነበሩ ከመሳፍንት ዘመን ጀምሮ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ሁሉ አልተደረገም።
2 ዜና መዋዕል 30:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሁለተኛውም ወር የቂጣውን በዓል ያደርጉ ዘንድ በኢየሩሳሌም ብዙ ሕዝብ ተሰበሰቡ፤ እጅግም ታላቅ ጉባኤ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሁለተኛው ወር የቂጣን በዓል ለማክበር እጅግ ብዙ ሕዝብ በኢየሩሳሌም ተሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሁለተኛውም ወር የቂጣውን በዓል ሊያከብር እጅግ ታላቅ ጉባኤ የሆነ ሕዝብ በኢየሩሳሌም ተሰበሰበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሁለተኛው ወር የቂጣን በዓል ለማክበር ብዙ ሰዎች በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሁለተኛውም ወር የቂጣውን በዓል ያደርግ ዘንድ እጅግ ታላቅ ጉባኤ የሆነ ሕዝብ በኢየሩሳሌም ተከማቸ። |
እንደዚህም ያለ ፋሲካ በእስራኤል ላይ ይፈርዱ ከነበሩ ከመሳፍንት ዘመን ጀምሮ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ሁሉ አልተደረገም።
ተነሥተውም በኢየሩሳሌም የነበሩትን መሠዊያዎችና ለጣዖታት የሚያጥኑበትን ዕቃ ሁሉ አስወገዱ፤ በቄድሮንም ወንዝ ጣሉት።
በሁለተኛውም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን በግ አረዱ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም ተዘጋጁ ነጹም። ወደ እግዚአብሔርም ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።
ኢዮስያስም ለአምላኩ ለእግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ፋሲካ አደረገ፤ በመጀመሪያውም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን በግ አረዱ።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእናንተ ወይም ከትውልዶቻችሁ ዘንድ ማንኛውም ሰው በሰውነቱ ቢረክስ፥ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ፥ ወይም በተወለዳችሁበት ሀገር ያለም ቢሆን እርሱ ደግሞ ለእግዚአብሔር ፋሲካን ያድርግ።