2 ዜና መዋዕል 29:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህናቱንና ሌዋውያኑንም አስመጣ፤ በምሥራቅ በኩል ባለው አደባባይም ሰበሰባቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህናቱንና ሌዋውያኑን አስገብቶ በምሥራቅ በኩል ባለው አደባባይ ላይ በመሰብሰብ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህናቱንና ሌዋውያኑንም አስመጣ፥ በምሥራቅ በኩል ባለው አደባባይም ሰበሰባቸው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህናትንና ሌዋውያንን በስተ ምሥራቅ በኩል በሚገኘው በቤተ መቅደሱ አደባባይ ሰበሰባቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህናቱንና ሌዋውያኑንም አስመጣ፤ በምስራቅ በኩል ባለው አደባባይም ሰበሰባቸው፤ |
እንዲህም አላቸው፥ “ሌዋውያን ሆይ፥ ስሙኝ፤ ራሳችሁን አንጹ፤ የአባቶቻችሁንም አምላክ የእግዚአብሔርን ቤት ቀድሱ፤ ርኩስን ነገር ሁሉ ከመቅደሱ አስወግዱ።
የጦር አለቆቹንም በሕዝቡ ላይ ሾመ፤ ሁሉንም በሸለቆው በኩል ባለው በከተማዪቱ በር አደባባይ ወደ እርሱ ሰበሰበ፤ እንዲህም ብሎ ልባቸውን አጸና፦
ከዚያም በኋላ የሄሜር ልጅ ሳዶቅ በቤቱ አንጻር ያለውን ሠራ። ከእርሱም በኋላ የምሥራቁ በር ጠባቂ የሴኬንያ ልጅ ሰማያ ሠራ።