መንገሥ በጀመረ ጊዜም የሃያ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የዘካርያስ ልጅ አቡ ትባል ነበር።
2 ዜና መዋዕል 29:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቱም ዳዊት እንዳደረገ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ፣ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቱም ዳዊት እንዳደረገ ሁሉ በጌታ ፊት ቅን ነገር አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቅያስ የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን መልካም ምሳሌነት በመከተል እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቱም ዳዊት እንዳደረገ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ። |
መንገሥ በጀመረ ጊዜም የሃያ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የዘካርያስ ልጅ አቡ ትባል ነበር።
እግዚአብሔርም ከኢዮሳፍጥ ጋር ነበረ፤ በፊተኛዪቱም በአባቱ በዳዊት መንገድ ሄዶአልና፥ ጣዖትንም አልፈለገምና፤
አካዝም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ፤ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አላደረገም።