La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 29:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ውስ​ጡም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ገብ​ተው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሁሉ፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊ​ያና ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የኅ​ብ​ስተ ገጹ​ንም ገበ​ታና ዕቃ​ውን ሁሉ አን​ጽ​ተ​ናል፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ገብተው እንዲህ አሉ፤ “የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በሙሉ፣ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ ከነዕቃዎቹ ሁሉ፣ ገጸ ኅብስቱ የሚቀመጥበትን ጠረጴዛ፣ ከነዕቃዎቹ አንጽተናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ውስጡም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ገብተው እንዲህ አሉት፦ “የጌታን ቤት ሁሉ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያና ዕቃውንም ሁሉ፥ የተቀደሰውም ሕብስት የሚቀመጥበትን ገበታና ዕቃውን ሁሉ አንጽተናል፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሌዋውያኑ ስለ ተከናወነው ሥራ ለንጉሥ ሕዝቅያስ የሚከተለውን መግለጫ አቀረቡ፦ “የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ፥ የተቀደሰው ኅብስት የሚቀመጥበትን ገበታና ከእነርሱም ጋር የተያያዙትን ሌሎች ዕቃዎች ጭምር ቤተ መቅደሱን በሙሉ አንጽተናል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ውስጡም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ገብተው “የእግዚአብሔርን ቤት ሁሉ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያና ዕቃውንም ሁሉ፥ የገጹንም ሕብስት ገበታና ዕቃውን ሁሉ አንጽተናል፤

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 29:18
6 Referencias Cruzadas  

በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ጣፋ​ጩን ዕጣን ያሳ​ር​ጋሉ፤ የገ​ጹ​ንም ኅብ​ስት በን​ጹሕ ገበታ ላይ፥ የወ​ር​ቁን መቅ​ረ​ዝና ቀን​ዲ​ሎ​ቹ​ንም ማታ ማታ እን​ዲ​ያ​በሩ ያዘ​ጋ​ጃሉ፤ እኛም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እን​ጠ​ብ​ቃ​ለን፤ እና​ንተ ግን ትታ​ች​ሁ​ታል።


በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ያነጹ ጀመር፤ በዚ​ያ​ውም ወር በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወለል ደረሱ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት በስ​ም​ንት ቀን አነጹ፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ ስድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈጸሙ።


ንጉ​ሡም አካዝ ነግሦ ሳለ በመ​ተ​ላ​ለፉ ያረ​ከ​ሰ​ውን ዕቃ ሁሉ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ናል፤ ቀድ​ሰ​ና​ልም፤ እነ​ሆም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ሆነ​ዋል” አሉት።


ርዝ​መ​ቱም ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም ዐሥር ክንድ የነ​በ​ረ​ውን የና​ሱን መሠ​ዊያ ሠራ።