La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 29:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሕዝ​ቅ​ያ​ስም የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ በነ​በረ ጊዜ መን​ገሥ ጀመረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የዘ​ካ​ር​ያስ ልጅ አብያ ትባል ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሕዝቅያስ በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዐምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ። እናቱ የዘካርያስ ልጅ ስትሆን፣ ስሟ አቢያ ይባል ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሕዝቅያስም የሀያ አምስት ዓመት ጎልማሳ በነበረ ጊዜ መንገሥ ጀመረ፥ በኢየሩሳሌም ሀያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የዘካርያስ ልጅ አቡ ትባል ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሕዝቅያስ ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ሲሆነው ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኻያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ፤ እናቱ አቢያ ተብላ የምትጠራ የዘካርያስ ልጅ ነበረች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሕዝቅያስም የሀያ አምስት ዓመት ጕልማሳ በነበረ ጊዜ መንገሥ ጀመረ፤ በኢየሩሳሌም ሀያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የዘካርያስ ልጅ አቡ ትባል ነበር።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 29:1
9 Referencias Cruzadas  

ልጁ አካዝ፥ ልጁ ሕዝ​ቅ​ያስ፥ ልጁ ምናሴ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መፍ​ራት ባስ​ተ​ማረ በዘ​ካ​ር​ያስ ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልግ ዘንድ ልብ አደ​ረገ፤ በዘ​መ​ኑም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነገ​ሩን አከ​ና​ወ​ነ​ለት።


አካ​ዝም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ነገር ግን ወደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አላ​ገ​ቡ​ትም፤ ልጁም ሕዝ​ቅ​ያስ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት በዖ​ዝ​ያ​ንና በኢ​ዮ​አ​ታም፥ በአ​ካ​ዝና በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን ስለ ይሁ​ዳና ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያየው የአ​ሞጽ ልጅ የኢ​ሳ​ይ​ያስ ራእይ።


የታ​መ​ኑ​ትን ሰዎች ካህ​ኑን ኦር​ያ​ንና የበ​ራ​ክ​ዩን ልጅ ዘካ​ር​ያ​ስን ምስ​ክ​ሮች አድ​ር​ግ​ልኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ አድ​ሮ​ባ​ቸ​ዋ​ልና፤”


በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት በዖ​ዝ​ያ​ንና በኢ​ዮ​አ​ታም በአ​ካ​ዝና በሕ​ዝ​ቅ​ያ​ስም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በኢ​ዮ​አስ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ዘመን ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።


በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታምና በአካዝ በሕዝቅያስም ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው፥ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው፥ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።