2 ዜና መዋዕል 28:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ቀበሩት፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ነገሥታት መቃብር አላገቡትም፤ ልጁም ሕዝቅያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አካዝ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በኢየሩሳሌምም ከተማ ተቀበረ፤ የተቀበረው ግን በእስራኤል ነገሥታት መካነ መቃብር አልነበረም። ልጁ ሕዝቅያስም በምትኩ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በከተማይቱም በኢየሩሳሌም ቀበሩት፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ነገሥታት መቃብር አላገቡትም፤ ልጁም ሕዝቅያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ አካዝ ሞተ፤ በኢየሩሳሌምም ተቀበረ፤ ይሁን እንጂ በነገሥታት መካነ መቃብር አልተቀበረም፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ሕዝቅያስ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በከተማይቱም በኢየሩሳሌም ቀበሩት፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ነገሥታት መቃብር አላገቡትም፤ ልጁም ሕዝቅያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ። |
እንዲህም ሆነ፤ የእስራኤል ንጉሥ የኤላ ልጅ ሆሴዕ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ ነገሠ።
ለእርሱም የኢዮሣፍጥ ልጆች አዛርያስ፥ ኢይሔል፥ ዘካርያስ፥ ዔዛርያስ፥ ሚካኤል፥ ሰፋጥያስ የሚባሉ ስድስት ወንድሞች ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጆች ነበሩ።
መንገሥም በጀመረ ጊዜ የሠላሳ ሁለት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ስምንት ዓመት ነገሠ፤ ማንም ሳያዝንለት ሄደ፤ በዳዊትም ከተማ እንጂ በነገሥታት መቃብር አልቀበሩትም።
ከእርሱም ዘንድ አልፈው ከሄዱ በኋላ እጅግ ታሞ ሳለ ተዉት፤ የገዛ ባሪያዎቹም ስለ ካህኑ ስለ ኢዮአዳ ልጅ ደም ተበቅለው በአልጋው ላይ ገደሉት፤ ሞተም፤ በዳዊትም ከተማ ቀበሩት፤ ነገር ግን በነገሥታት መቃብር አልቀበሩትም።
ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ለምጻም ነው ብለዋልና የነገሥታቱ መቃብር ባልሆነ እርሻ ውስጥ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
ሕዝቅያስም የሃያ አምስት ዓመት ጐልማሳ በነበረ ጊዜ መንገሥ ጀመረ፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የዘካርያስ ልጅ አብያ ትባል ነበር።
ቍጥሩ ከባሕር አሸዋ የሚበልጥ በደልን በድያለሁና፥ ኀጢአቴም ብዙ ነውና፤ ከበደሌም ብዛት የተነሣ ቀና ብዬ የሰማይን ርዝመት አይ ዘንድ አገባቤ አይደለም። ሰውነቴን ከኀጢአቴ አሳርፋት ዘንድ በብረት ቀፎ ደከምሁ፤ በዚህም ደግሞ አላረፍሁም፤ መዓትህን አነሣሥቻለሁና፥
ስለዚህም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት፤ ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤ አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም።