“ደግሞም በእግዚአብሔር ፊት በእኛ ላይ በደል ታመጡብናላችሁና፥ ኀጢአታችንንና በደላችንን ታበዙብናላችሁና የተማረኩትን ወደዚህ አታግቡ፤ በደላችን ታላቅ ነውና፥ የእግዚአብሔርም የመቅሠፍቱ ቍጣ በእስራኤል ላይ ነውና” አሉአቸው።
2 ዜና መዋዕል 28:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰልፈኞቹም ምርኮኞቹንና ምርኮውን በአለቆችና በጉባኤ ሁሉ ፊት ተዉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ወታደሮቹ በሹማምቱና በጉባኤው ሁሉ ፊት ምርኮኞቹን ለቀቁ፤ የተማረከውንም ዕቃ መለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተዋጊዎቹም ምርኮኞቹንና ምርኮውን በአለቆችና በጉባኤው ሁሉ ፊት ተው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሠራዊቱ እስረኞቹንና ምርኮውን ለሕዝቡና ለመሪዎቻቸው አስረከቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰልፈኞቹም ምርኮኞቹንና ምርኮውን በአለቆችና በጉባኤው ሁሉ ፊት ተው። |
“ደግሞም በእግዚአብሔር ፊት በእኛ ላይ በደል ታመጡብናላችሁና፥ ኀጢአታችንንና በደላችንን ታበዙብናላችሁና የተማረኩትን ወደዚህ አታግቡ፤ በደላችን ታላቅ ነውና፥ የእግዚአብሔርም የመቅሠፍቱ ቍጣ በእስራኤል ላይ ነውና” አሉአቸው።
በስማቸውም የተጻፉ ሰዎች ተነሥተው ምርኮኞቹን ወሰዱ፤ በመካከላቸውም ራቁታቸውን ለነበሩት ሁሉ ከምርኮው አለበሱአቸው፤ አጐናጸፉአቸውም፤ ጫማም በእግራቸው አደረጉላቸው፤ መገቡአቸውም፤ አጠጡአቸውም፤ ቀቡአቸውም፤ ደካሞቹንም ሁሉ በአህዮች ላይ አስቀመጡአቸው፤ ዘንባባም ወዳለበት ከተማ ወደ ኢያሪኮ ወደ ወንድሞቻቸው አመጡአቸው፤ ወደ ሰማርያም ተመለሱ።
እነርሱም፥ “እንመልስላቸዋለን፤ ከእነርሱም ምንም አንሻም፤ እንደተናገርህ እንዲሁ እናደርጋለን” አሉ። ካህናቱንም ጠርቼ እንደዚህ ነገር ያደርጉ ዘንድ አማልኋቸው።