የአሞንም ልጆች የዳዊት ሰዎች እንዳፈሩ ባዩ ጊዜ ሐናን የአሞን ልጆች ንጉሥ ከሶርያ መስጴጦምያ፥ ከሶርያ ሞዓካ፥ ከሱባም ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን ይቀጥሩ ዘንድ አንድ ሺህ መክሊት ብር ላከ።
2 ዜና መዋዕል 25:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ከእስራኤል ዘንድ መቶ ሺህ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎችን በመቶ መክሊት ብር ቀጠረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም በመቶ መክሊት ጥሬ ብር አንድ መቶ ሺሕ ተዋጊዎች ከእስራኤል ቀጠረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ከእስራኤል ዘንድ መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎችን በመቶ መክሊት ብር ቀጠረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሜስያስ በተጨማሪ በሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ጥሬ ብር ከእስራኤል አንድ መቶ ሺህ ወታደሮችን ቀጠረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ከእስራኤል ዘንድ መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን በመቶ መክሊት ብር ቀጠረ። |
የአሞንም ልጆች የዳዊት ሰዎች እንዳፈሩ ባዩ ጊዜ ሐናን የአሞን ልጆች ንጉሥ ከሶርያ መስጴጦምያ፥ ከሶርያ ሞዓካ፥ ከሱባም ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን ይቀጥሩ ዘንድ አንድ ሺህ መክሊት ብር ላከ።
ንጉሡ አሜስያስም የይሁዳን ሕዝብ ሰበሰበ፤ እንደ እየአባቶቻቸውም ቤቶች አቆማቸው፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ሁሉ የሽህ አለቆችንና የመቶ አለቆችን አደረገ፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉትን ሁሉ ቈጠረ፤ ለሰልፍም የሚወጡ፥ ጋሻና ጦርም የሚይዙ ሦስት መቶ ሺህ የተመረጡ ሰዎችን አገኘ።
አንድ የእግዚአብሔር ሰው ግን ወደ እርሱ መጥቶ፥ “ንጉሥ ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእስራኤልና ከኤፍሬም ልጆች ሁሉ ጋር አይደለምና የእስራኤል ጭፍራ ከአንተ ጋር አይውጣ።