የቀረውም የኢዮርብዓም ነገር፥ እንዴት እንደ ተዋጋ፥ እንዴትም እንደ ነገሠ፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።
2 ዜና መዋዕል 25:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀሩትም የፊተኞቹና የኋለኞቹ የአሜስያስ ነገሮች፥ እነሆ፥ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአሜስያስ ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የተከናወነው ሌላው ተግባር ሁሉ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀረውም የፊተኛውና የኋላኛው የአሜስያስ ነገር፥ እነሆ፥ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሜስያስ በዘመነ መንግሥቱ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀረውም የፊተኛውና የኋላኛው የአሜስያስ ነገር፥ እነሆ፥ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? |
የቀረውም የኢዮርብዓም ነገር፥ እንዴት እንደ ተዋጋ፥ እንዴትም እንደ ነገሠ፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።
የቀረውም ያደረገው የዮአስ ነገር፥ ኀይሉም፥ ከይሁዳም ንጉሥ ከአሜስያስ ጋር እንደ ተዋጋ፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባለራእዩ በሳሙኤል ታሪክ፥ በነቢዩም በናታን ታሪክ፥ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፎአል።
የቀረውም የፊተኞቹና የኋለኞቹ የኢዮሣፍጥ ነገሮች፥ እነሆ የእስራኤልን ነገሥታት ታሪክ በጻፈው በአናኒ ልጅ በነቢዩ በኢዩ ታሪክ ተጽፈዋል።
የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ ከእስራኤል ንጉሥ ከኢዮአካዝ ልጅ ከኢዮአስ ሞት በኋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ።
አሜስያስም እግዚአብሔርን ከመከተል በራቀ ጊዜ በኢየሩሳሌም የዐመፅ መሐላ አደረጉበት፤ ወደ ለኪሶም ኮበለለ፤ በስተኋላውም ወደ ለኪሶ ላኩ፤ በዚያም ገደሉት።
የቀሩትም የኢዮአታም ነገሮች፥ ሰልፉም ሁሉ፥ ሥራውም፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።
የሕዝቅያስም የቀሩት ነገሮች፥ ቸርነቱም፥ እነሆ፥ በአሞጽ ልጅ በነቢዩ በኢሳይያስ ራእይ በይሁዳና በእስራኤልም ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
የቀሩትም የኢዮአቄም ነገሮች፥ ያደረገውም ርኵሰት፥ በእርሱም የተገኘው ሁሉ፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል፤ ኢዮአቄምም እንደ አባቶቹ አንቀላፋ፤ ከአባቶቹም ጋር በጋኖዛን ከተማ ተቀበረ። ልጁም ኢኮንያን ከእርሱ ቀጥሎ ነገሠ።