ዳዊትም የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ ያመጣት ዘንድ አልወደደም፤ ዳዊትም በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት አገባት።
2 ዜና መዋዕል 25:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወርቁንና ብሩን ሁሉ፥ በእግዚአብሔርም ቤት በአብዲዶም እጅ የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ፥ በንጉሡም ቤተ መዛግብት የተገኘውን፥ በመያዣ የተያዙትንም ልጆች ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በአቢዳራ ጥበቃ ሥር የነበረውንና በአምላክ ቤተ መቅደስ የተገኘውን ወርቅ፣ ጥሬ ብርና ዕቃ በሙሉ፣ ከቤተ መንግሥቱም ንብረትና በመያዣ ከያዛቸው ሰዎች ጭምር ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወርቁንና ብሩን ሁሉ፥ በጌታም ቤት ከዖቤድኤዶም ጋር የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ፥ የንጉሡም ቤት መዛግብት፥ በመያዣ የተያዙትንም ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ መቅደስ የነበረውን ወርቅና ብር ሁሉ፥ በዖቤድኤዶም ዘሮች ይጠበቁ የነበሩትን የቤተ መቅደሱን ዕቃዎችና የቤተ መንግሥቱን ሀብት በሙሉ ምርኮ አድርጎ በመያዣም ስም የወሰዳቸውን ሰዎች በመውሰድ ወደ ሰማርያ ይዞ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወርቁንና ብሩን ሁሉ፥ በእግዚአብሔርም ቤት ከዖቤድኤዶም ጋር የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ፥ የንጉሡም ቤት መዛግብት፥ በመያዣ የተያዙትንም ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ። |
ዳዊትም የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ ያመጣት ዘንድ አልወደደም፤ ዳዊትም በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት አገባት።
ወርቁንና ብሩን ሁሉ፥ በእግዚአብሔርም ቤትና በንጉሥ ቤተ መዛግብት የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ፤ በመያዣም የተያዙትን ልጆች ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ።
የግብፅ ንጉሥ ሱስቀምም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ የእግዚአብሔርንም ቤተ መዛግብትና የንጉሡን ቤተ መዛግብት ወሰደ፤ ሁሉንም ወሰደ፤ ደግሞም ሰሎሞን የሠራቸውን የወርቁን አላባሽ አግሬ ጋሻዎችን ወሰደ።