የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአስ አባቶቹ የይሁዳ ነገሥታት ኢዮሣፍጥና ኢዮራም፥ አካዝያስም የቀደሱትን ቅዱስ ነገር፥ እርሱም የቀደሰውን፥ በእግዚአብሔርም ቤትና በንጉሡም ቤተ መዛግብት የተገኘውን ወርቅ ሁሉ ወሰደ፤ ወደ ሶርያም ንጉሥ ወደ አዛሄል ላከው። እርሱም ከኢየሩሳሌም ተመለሰ።
2 ዜና መዋዕል 24:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የልጆቹና በእርሱ ላይ የተደረገው ነገር፥ የእግዚአብሔርንም ቤት ማደሱ፥ እነሆ በነገሥታቱ የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል። ልጁም አሜስያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወንዶች ልጆቹ ታሪክ፣ ስለ እርሱ የተነገሩት ብዙ ትንቢቶችና የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መታደስ በነገሥታቱ የታሪክ መዛግብት ተጽፈዋል። ልጁ አሜስያስም በርሱ ፈንታ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የልጆቹና በእርሱ ላይ የተደረገው ነገር የጌታንም ቤት ማደሱ፥ እነሆ፥ በነገሥታቱ መጽሐፍ ተጽፎአል። ልጁም አሜስያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢዮአስ ልጆች ታሪክ፥ በኢዮአስ ላይ ተነግረው የነበሩት የትንቢት ቃላትና ኢዮአስ ቤተ መቅደሱን እንዴት እንዳደሰ በነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ መግለጫ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሜስያስ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የልጆቹና በእርሱ ላይ የተደረገው ነገር የእግዚአብሔርንም ቤት ማደሱ፥ እነሆ፥ በነገሥታቱ መጽሐፍ ተጽፎአል። ልጁም አሜስያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ። |
የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአስ አባቶቹ የይሁዳ ነገሥታት ኢዮሣፍጥና ኢዮራም፥ አካዝያስም የቀደሱትን ቅዱስ ነገር፥ እርሱም የቀደሰውን፥ በእግዚአብሔርም ቤትና በንጉሡም ቤተ መዛግብት የተገኘውን ወርቅ ሁሉ ወሰደ፤ ወደ ሶርያም ንጉሥ ወደ አዛሄል ላከው። እርሱም ከኢየሩሳሌም ተመለሰ።
አገልጋዮቹም የኢያሙሃት ልጅ ኢያዜክርና የሳሜር ልጅ ኢያዛብድ መቱት፤ ሞተም፤ በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት፤ ልጁም አሜስያስ በፋንታው ነገሠ።
የቀረውም የፊተኞቹና የኋለኞቹ የኢዮሣፍጥ ነገሮች፥ እነሆ የእስራኤልን ነገሥታት ታሪክ በጻፈው በአናኒ ልጅ በነቢዩ በኢዩ ታሪክ ተጽፈዋል።
ንጉሡና ኢዮአዳም በእግዚአብሔር ቤት ሥራ ላይ ለተሾሙት ሰጡአቸው፤ እነርሱም የእግዚአብሔርን ቤት የሚጠግኑትን ጠራቢዎችንና አናጢዎችን፥ የእግዚአብሔርንም ቤት የሚያድሱትን የብረትና የናስ ሠራተኞችን ይቀጥሩበት ነበር።
አሜስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እናቱ ኢዮዓዲን የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች።
የቀረውም ፊተኛውና ኋለኛው የሰሎሞን ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ፥ በሴሎናዊውም በአኪያ ትንቢት፥ ስለ ናባጥም ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው በባለ ራእዩ በኢዩሔል ራእይ የተጻፈ አይደለምን?