መቶ አለቆቹንና ኮራውያንን፥ ዘበኞችንና የሀገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰዳቸው፤ ንጉሡንም ከእግዚአብሔር ቤት አወጣው፤ በዘበኞችም በር መንገድ ወደ ንጉሡ ቤት አመጡት፤ በነገሥታቱም ዙፋን አስቀመጡት።
2 ዜና መዋዕል 23:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመቶ አለቆችንም፥ ከበርቴዎችንም፥ የሕዝቡንም አለቆች፥ የሀገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰደ፤ ንጉሡንም ከእግዚአብሔር ቤት አወረዱት፤ በእግዚአብሔርም ቤት በውስጠኛው በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት አመጡት፤ ንጉሡንም በመንግሥቱ ዙፋን ላይ አስቀመጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመቶ አለቆቹን፣ መኳንንቱን፣ የሕዝቡን ገዦችና የአገሩን ሕዝብ ሁሉ ይዞ ንጉሡን ከላይ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወደ ታች አመጣው። በላይኛውም መግቢያ በኩል ወደ ቤተ መንግሥቱ ገብተው ንጉሡን በመንግሥቱ ዙፋን ላይ አስቀመጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመቶ አለቆችንም፥ ከበርቴዎቹንም፥ የሕዝቡንም አለቆች፥ የአገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰደ፥ ንጉሡንም ከጌታ ቤት ወስደው በላይኛው በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት መጡ፥ ንጉሡንም በመንግሥቱ ዙፋን ላይ አስቀመጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጦር መኰንኖቹ፥ የታወቁ የአገር ሽማግሌዎች የመንግሥት ባለሥልጣኖችና የቀሩትም ሕዝብ ሁሉ ከዮዳሄ ጋር በመሆን ከቤተ መቅደስ እስከ ቤተ መንግሥት ድረስ ንጉሡን አጅበው ሄዱ፤ በቤተ መንግሥቱም ዋና በር ገቡ፤ ንጉሡም በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመቶ አለቆችንም፥ ከበርቴዎቹንም፥ የሕዝቡንም አለቆች፥ የአገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰደ፤ ንጉሡንም ከእግዚአብሔር ቤት አወረደ፤ በላይኛውም በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት መጡ፤ ንጉሡንም በመንግሥቱ ዙፋን ላይ አኖሩት። |
መቶ አለቆቹንና ኮራውያንን፥ ዘበኞችንና የሀገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰዳቸው፤ ንጉሡንም ከእግዚአብሔር ቤት አወጣው፤ በዘበኞችም በር መንገድ ወደ ንጉሡ ቤት አመጡት፤ በነገሥታቱም ዙፋን አስቀመጡት።
ነገር ግን የጣዖታቱን ቤት አላስወገደም፤ ሕዝቡም ገና በኮረብቶች ላይ ይሠዉና ያጥኑ ነበር። እርሱም የላይኛውን የእግዚአብሔርን ቤት በር ሠራ።