ኤልያስም ሕዝቡን፥ “የበዓልን ነቢያት ያዙ፤ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳን የሚያመልጥ አይኑር፤” አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየወጋ ጣላቸው።
2 ዜና መዋዕል 23:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገለልም ብለው አሳለፉአት፤ እርስዋም ወደ ፈረሱ በር መግቢያ ወደ ንጉሡ ቤት ሄደች፤ በዚያም ገደሉአት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም በቤተ መንግሥቱ ግቢ የፈረስ መግቢያ በር ወደተባለው ቦታ እንደ ደረሰች ያዟት፤ በዚያም ገደሏት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጃቸውን በእስዋ ላይ ጭነው ያዝዋት፤ እርሷም ወደ ፈረሱ በር መግቢያ ወደ ንጉሡ ቤት ሄደች፥ በዚያም ገደሉአት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እርስዋን አፈፍ አድርገው በመያዝ ወደ ቤተ መንግሥት ወሰዱአት፤ እዚያም “የፈረስ መግቢያ ቅጽር በር” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ገደሉአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገለልም ብለው አሳለፉአት፤ እርስዋም ወደ ፈረሱ በር መግቢያ ወደ ንጉሡ ቤት ሄደች፤ በዚያም ገደሉአት። |
ኤልያስም ሕዝቡን፥ “የበዓልን ነቢያት ያዙ፤ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳን የሚያመልጥ አይኑር፤” አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየወጋ ጣላቸው።
ካህኑም ኢዮአዳ ወጥቶ በጭፍራው ላይ የተሾሙትን አለቆችና የመቶ አለቆች፥ “ከቤተ እግዚአብሔር ወደ ውጭ አውጡአት፤ የሚከተላትም በሰይፍ ይገደል” ብሎ አዘዛቸው። ካህኑ፥ “በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አትገደል” ብሎአልና።
የአስሬሞትም ሸለቆ ሁሉ እስከ ቄድሮን ወንዝ ድረስ በምሥራቅ በኩል እስካለው እስከ ፈረስ በር ማዕዘን ድረስ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ከእንግዲህም ወዲህ ለዘለዓለም አይነቀልም፤ አይፈርስምም።
ምድርን የሚያረክሳት ደም ነውና የምትኖሩባትን ምድር በነፍስ ግድያ አታርክሷት። ምድሪቱም በደም አፍሳሹ ደም ካልሆነ በቀር ከፈሰሰባት ደም አትነጻም።
አዶኒቤዜቅም፥ “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡ ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ በታች ፍርፋሪ ይለቅሙ ነበሩ፤ እኔ እንዳደረግሁ እግዚአብሔር እንዲሁ መለሰልኝ” አለ። ወደ ኢየሩሳሌምም ወሰዱት፥ በዚያም ሞተ።