ዳዊትና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣሪያዎች በበገናና በመሰንቆ፥ በከበሮና በነጋሪት፥ በጸናጽልና በዕንዚራ በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይጫወቱ ነበር።
2 ዜና መዋዕል 20:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በበገናና በመሰንቆ፥ በመለከትም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ቤት ገቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ እንደ ገቡም በበገና፣ በመሰንቆና በመለከት ድምፅ ታጅበው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በበገናና በመሰንቆ በመለከትም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ጌታ ቤት ገቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜም በእምቢልታ፥ በዋሽንትና በበገና ድምፅ እየታጀቡ በሰልፍ ወደ ቤተ መቅደስ ገቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በበገናና በመሰንቆ በመለከትም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ቤት ገቡ። |
ዳዊትና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣሪያዎች በበገናና በመሰንቆ፥ በከበሮና በነጋሪት፥ በጸናጽልና በዕንዚራ በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይጫወቱ ነበር።
ዳዊትና እስራኤል ሁሉ ከመዘምራን ጋር በበገና፥ በመሰንቆና በከበሮ፥ በጸናጽልና በመለከት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይዘምሩ ነበር።
እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና፥ በመሰንቆም ከአባታቸው ጋራ የእግዚአብሔርን ቤት ለማገልገል ወደ ንጉሡ ቀርበው ያመሰግኑ ነበር። አሳፍም ኤዶትምም ኤማንም ያመሰግኑ ነበር።
የይሁዳ ሰዎች ሁሉ፥ ንጉሣቸውም ኢዮሣፍጥ፥ እግዚአብሔር በጠላቶቻቸው ላይ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
እግዚአብሔር የእስራኤልን ጠላቶች እንደ ወጋ በሰሙ ጊዜ በምድር ነገሥታት ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ፍርሀት ሆነ።