2 ዜና መዋዕል 18:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነቢዩ ሚክያስም፥ “ውጣ፤ ተከናወን፤ በእጅህም አልፈው ይሰጣሉ” አለ። ንጉሡም፥ “በእግዚአብሔር ስም ከእውነት በቀር እንዳትነግረኝ ስንት ጊዜ አምልሃለሁ?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም፣ “ከእውነት በቀር ምንም ነገር በእግዚአብሔር ስም እንዳትነግረኝ የማምልህ ስንት ጊዜ ነው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም፦ “በጌታ ስም ከእውነት በቀር ምንም ዓይነት ነገር እንዳትነግረኝ ስንት ጊዜ አምልሃለሁ?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አክዓብም “በእግዚአብሔር ስም ከእውነት በቀር እንዳትነግረኝ ብዬ የማስምልህ ስንት ጊዜ ነው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም “በእግዚአብሔር ስም ከእውነት በቀር እንዳትነግረኝ ስንት ጊዜ አምልሃለሁ?” አለው። |
እርሱም፥ “እስራኤል ሁሉ ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበትነው አየሁ፤ እግዚአብሔርም፦ ለእነዚህ ጌታ የላቸውም፥ እያንዳንዱም በሰላም ወደ ቤቱ ይመለስ አለ” ብሎ ተናገረ።
ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለው።
በታላቅ ድምፅም እየጮኸ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለ፤
ከአይሁድም አስማት እያደረጉ የሚዞሩ ሰዎች ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ “ጳውሎስ በሚያስተምርበት በኢየሱስ ስም እናምላችኋለን” እያሉ የጌታችን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ነበር።
ሳኦልም በዚያ ቀን ትልቅ በደል ፈጸመ፤ “ጠላቶቼን እስክበቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚበላ ሰው ርጉም ይሁን” ብሎ ሕዝቡን አምሎአቸው ነበርና። ሕዝቡም ሁሉ እህል አልቀመሱም። ሀገሩም ሁሉ ምሳ አልበላም።