ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን በእግር በእግራቸው ተከትለው አባረሩአቸው፤ ፍልስጥኤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንንና አሚናዳብን ሜልኪሳንም ገደሉ።
1 ዜና መዋዕል 9:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኔርም ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሜልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስበኣልን ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኔርም ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፣ ሜልኪሳን፣ አሚናዳብን፣ አስበኣልን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኔርም ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሜልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስባኣልን ወለደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ንጉሥ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታን፥ ማልኪሹዓ፥ አቢናዳብና ኤሽባዓል ተብለው የሚጠሩትን ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኔርም ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሜልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስባኣልን ወለደ። |
ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን በእግር በእግራቸው ተከትለው አባረሩአቸው፤ ፍልስጥኤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንንና አሚናዳብን ሜልኪሳንም ገደሉ።
ሜቅሎትም ሳምአን ወለደ፤ እነርሱም ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው መካከል ይቀመጡ ነበር።
ስለዚህም በማኪማስ ጦርነት ጊዜ ሰይፍና ጦር ከሳኦልና ከዮናታን ጋር በነበሩ ሕዝብ ሁሉ እጅ አልተገኘም፤ ብቻ በሳኦልና በልጁ በዮናታን ዘንድ ተገኘ።
በነጋም ጊዜ፥ የሳኦል ልጅ ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፤ በዚያ በኩል ወዳለው ወደ ፍልስጥኤማውያን ሰፈር እንለፍ” አለው፤ ለአባቱም አልነገረውም።
ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን ተከትለው አገኙአቸው። ፍልስጥኤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንንና አሚናዳብን፥ ሜልኪሳንም ገደሉአቸው።