ካህኑም ዮዳሄ በጭፍራው ላይ የተሾሙትን የመቶ አለቆች፥ “ወደ ሰልፉ መካከል አውጡአት፤ የሚከተላትንም በሰይፍ ግደሉት” ብሎ አዘዛቸው፤ ካህኑ፥ “በእግዚአብሔር ቤት አትገደል” ብሎአልና።
1 ዜና መዋዕል 9:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱ ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፤ የድንኳኑንም መድረክ ይጠብቁ ነበር። አባቶቻቸውም የእግዚአብሔርን ሰፈር መግቢያ ይጠብቁ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቆሬ ልጅ የአብያሳፍ ልጅ፣ የቆሬ ልጅ ሰሎምና ከርሱም ቤተ ሰብ የሆኑት ቆሬያውያን ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ እንደ ነበር ሁሉ፣ እነዚህም ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱም ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፥ አባቶቻቸውም የጌታን ሰፈር መግቢያ ይጠብቁ እንደ ነበር እንዲሁ የድንኳኑን የመግቢያ ደጅ ይጠብቁ ነበር።። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኤቢያሳፍ የልጅ ልጅ የቆሬ ልጅ ሻሉም የቆሬ ጐሣ አባሎች ከሆኑት ከሌሎች ዘመዶቹ ጋር በመሆን የቀድሞ አባቶቻቸው የእግዚአብሔርን ሰፈር ይጠብቁ በነበረው ዐይነት እግዚአብሔር ወደሚመለክበት ድንኳን የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱም ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፤ የድንኳንኑም መድረክ ይጠብቁ ነበር። አባቶቻቸውም የእግዚአብሔርን ሰፈር መግቢያ ጠብቀው ነበር። |
ካህኑም ዮዳሄ በጭፍራው ላይ የተሾሙትን የመቶ አለቆች፥ “ወደ ሰልፉ መካከል አውጡአት፤ የሚከተላትንም በሰይፍ ግደሉት” ብሎ አዘዛቸው፤ ካህኑ፥ “በእግዚአብሔር ቤት አትገደል” ብሎአልና።
መቶ አለቆችም ብልሁ ዮዳሄ ያዘዛቸውን ሁሉ አደረጉ፤ ከእነርሱም እያንዳንዱ በሰንበት ይገቡ የነበሩትን፥ በሰንበትም ይወጡ የነበሩትን ሰዎች ይዘው ወደ ካህኑ ወደ ዮዳሄ መጡ።
በሣጥኑም ውስጥ የተገኘው ወርቅ ብዙ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ የንጉሡ ጸሓፊና የካህናቱ አለቃ ይመጡ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን ገንዘብ ሁሉ ቈጥረው በከረጢት ውስጥ ያኖሩት ነበር።
ወደ እግዚአብሔርም ቤት በበረኛው በሰሎም ልጅ በማሴው ጓዳ በላይ ባለው በአለቆቹ ጓዳ አጠገብ ወደ አለው ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ጎዶልያ ልጅ ወደ ሐናንያ ልጆች ጓዳ አገባኋቸው።