ሌዋውያኑም የኢዩኤልን ልጅ ኤማንን፥ ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፥ ከወንድሞቻቸውም ከሜራሪ ልጆች የቂሳንን ልጅ ኢታንን፥
1 ዜና መዋዕል 6:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጁ ተአት፥ ልጁ ኡርኤል፥ ልጁ ዖዝያ፥ ልጁ ሳውል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጁ ታሐት፣ ልጁ ኡርኤል፣ ልጁ ዖዝያ፣ ልጁ ሳውል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጁ ኢኢት፥ ልጁ ኡርኤል፥ ልጁ ዖዝያ፥ ልጁ ሳውል ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሲር ታሐትን ወለደ፤ ታሐት ኡሪኤልን ወለደ፤ ኡሪኤል ዑዚያን ወለደ፤ ዑዚያም ሻኡልን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጁ ታሐት፥ ልጁ ኡርኤል፥ ልጁ ዖዝያ፥ ልጁ ሳውል። |
ሌዋውያኑም የኢዩኤልን ልጅ ኤማንን፥ ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፥ ከወንድሞቻቸውም ከሜራሪ ልጆች የቂሳንን ልጅ ኢታንን፥
አለቃውም አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም ቀጥሎ ዘካርያስ፥ ኢያሔል፥ ሰሜራሞት፥ ይሔኤል፥ ማታትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ አብዲዶም፥ ይዒኤል በመሰንቆና በበገና፥ አሳፍም በጸናጽል ይዘምሩ ነበር።
በቀባቃር፥ ኤሬስ፥ ጋላል፥ የአሳፍ ልጅ የዝክሪ ልጅ የሜካ ልጅ ማታንያስ፤ የኤዶታም ልጅ የጋላል ልጅ የሰማያ ልጅ አብድያ፤