በእነዚያም ወራት ረዓይት በምድር ላይ ነበሩ። ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሰው ሴቶች ልጆች በገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው፤ እነርሱም በዱሮ ዘመን ስማቸውን ያስጠሩ ኀያላን ሰዎች ሆኑ።
1 ዜና መዋዕል 4:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ በስማቸው የተጠሩ በወገኖቻቸው ላይ አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸውም ቤቶች በዝተው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ሰዎች የየጐሣቸው መሪዎች ነበሩ። የየቤተ ሰባቸውም ብዛት እጅግ በጣም እየጨመረ ሄደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ በስማቸው የተጠሩ በወገኖቻቸው ላይ አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸውም ቤቶች እጅግ በዝተው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነዚህም ቤተሰብ እየበዛ ሄደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ በስማቸው የተጠሩ በወገኖቻቸው ላይ አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸውም ቤቶች በዝተው ነበር። |
በእነዚያም ወራት ረዓይት በምድር ላይ ነበሩ። ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሰው ሴቶች ልጆች በገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው፤ እነርሱም በዱሮ ዘመን ስማቸውን ያስጠሩ ኀያላን ሰዎች ሆኑ።
የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፥ ይስዔ፥ ኤሊኤል፥ ዓዝርኤል፥ ኢይርምያ፥ ሆዳይዋ፥ ኢየድኤል፤ እነርሱ ጽኑዓን ኀያላን የታወቁ ሰዎች የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች ነበሩ።