1 ዜና መዋዕል 4:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንደሮቻቸውም ሁሉ እስከ በኣል ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ነበሩ። መቀመጫቸውና ድርሻቸውም ይህ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነዚህም ከተሞች ዙሪያ እስከ ባኣል የሚዘልቁ መንደሮች ነበሩ፤ መኖሪያቸው በዚሁ ሲሆን። የትውልድ መዝገብም አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስከ በኣልም ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ የነበሩ መንደሮቻቸው ሁሉ ነበሩ። መቀመጫቸውና የትውልዳቸው መዝገቦች እነዚህ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአካባቢያቸው በሚገኙ መንደሮች ይኖሩ ነበር፤ ይህም እነርሱ የሚኖሩበት ስፍራ እስከ ባዕላት ከተማ ይዘልቅ ነበር። እንግዲህ የስምዖን ዘሮች ስለ ቤተሰቦቻቸውና ስለሚኖሩባቸው ስፍራዎች መዝግበው ያቈዩት ጽሑፍ ይህ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስከ በኣልም ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ የነበሩ መንደሮቻቸው ሁሉ ነበሩ። መቀመጫቸውና የትውልዳቸው መዝገቦች እነዚህ ናቸው። |
በስማቸው የተጻፉ እነዚህም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰማሪያ ነበርና በስፍራቸው ተቀመጡ።
እስከ ባሌቅ ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ያሉ መንደሮቻቸው ሁሉ ናቸው። ይህም በባሜት ላይ ወደ ደቡብ ያልፋል። የስምዖን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።