1 ዜና መዋዕል 4:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮፎኒም ልጅ የካሌብ ልጆች ዔሩ፥ ኤላ፥ ነዓም ነበሩ። የኤላም ልጅ ቄኔዝ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮፎኒ ልጅ የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ ዒሩ፣ ኤላ፣ ነዓም። የኤላ ልጅ፤ ቄኔዝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮፎኒም ልጅ ካሌብ ልጆች ዒሩ፥ ኤላ፥ ነዓም ነበሩ፤ የኤላም ልጅ ቄኔዝ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይፉኔ ልጅ ካሌብም ዒሩ፥ ኤላና ናዓም ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ኤላም ቀናዝን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮፎኒም ልጅ የካሌብ ልጆች ዒሩ፥ ኤላ፥ ነዓም ነበሩ። |
ወዳጄ ካሌብ ግን ሌላ መንፈስ በእርሱ ላይ ስለ ሆነና ስለ ተከተለኝ እርሱ ወደ ገባባት ምድር አገባዋለሁ፤ ዘሩም ይወርሳታል።
ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር በእርስዋ አስቀምጣችሁ ዘንድ እጄን ዘርግቼ ወደ ማልሁላችሁ ምድር በእውነት እናንተ አትገቡም።