ሄደሽ ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ግቢና፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ለእኔ ለአገልጋይህ፦ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል ብለህ አልማልህልኝምን? ስለምንስ አዶንያስ ይነግሣል? በዪው።
1 ዜና መዋዕል 28:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ብዙ ልጆች ሰጥቶኛል፤ ከወንዶቹ ልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ሁሉ ላይ እንዲነግሥ ደግሞ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በጌታ መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ እንዲነግሥ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእኔም ብዙ ወንዶች ልጆችን ሰጠኝ፤ ነገር ግን የሚቀጥለው የእስራኤል ንጉሥ ይሆን ዘንድ የመረጠው ልጄን ሰሎሞንን ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል። |
ሄደሽ ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ግቢና፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ለእኔ ለአገልጋይህ፦ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል ብለህ አልማልህልኝምን? ስለምንስ አዶንያስ ይነግሣል? በዪው።
አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ከአንተ በኋላ በጌታዬ በንጉሥ ዙፋን ላይ የሚቀመጠውን ትነግራቸው ዘንድ የእስራኤል ሁሉ ዐይን ይመለከትሃል።
በእውነት፦ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፤ በእኔም ፋንታ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል ብዬ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር እንደ ማልሁልሽ፥ እንዲሁ ዛሬ በእውነት አደርጋለሁ።”
በኋላውም ተከትላችሁ ውጡ፤ እርሱም መጥቶ በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ፤ በእኔም ፋንታ ይንገሥ፤ በእስራኤልና በይሁዳም ላይ ይነግሥ ዘንድ አዝዣለሁ።”
እርሱም፥ “መንግሥቱ ለእኔ እንደ ነበረ፥ እስራኤልም ሁሉ ንጉሥ እሆን ዘንድ ፊታቸውን ወደ እኔ አድርገው እንደ ነበረ አንቺ ታውቂያለሽ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖለታልና መንግሥት ተመልሳ ለወንድሜ ሆናለች።
እግዚአብሔርም የተናገረውን ቃል አጸና፤ እግዚአብሔርም ተስፋ እንደ ሰጠ በአባቴ በዳዊት ፋንታ ተነሣሁ፤ በእስራኤልም ዙፋን ላይ ተቀመጥሁ፤ ለእስራኤልም አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ሠራሁ።
ንጉሡ ዳዊትም ለጉባኤው ሁሉ እንዲህ አለ፥ “እግዚአብሔር ብቻውን የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ለጋ ብላቴና ነው፤ ሕንጻው ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክ ነው እንጂ ለሰው አይደለምና ሥራው ታላቅ ነው።
በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ንጉሥ እንድትሆን በዙፋኑ ላይ ያስቀምጥህ ዘንድ የወደደህ አምላክህ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን፤ አምላክህ እግዚአብሔር እስራኤልን ለዘለዓለም ያጸናቸው ዘንድ ወድዶአቸዋልና ስለዚህ ፍርድንና ጽድቅን ታደርግ ዘንድ በላያቸው አነገሠህ።”
ከወንድሞችህ መካከል አምላክህ እግዚአብሔር የመረጠውን ለአንተ አለቃ ትሾማለህ፤ ወንድምህ ያልሆነውን ሌላ ሰው በአንተ ላይ መሾም አትችልም።