1 ዜና መዋዕል 27:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቈላውም ውስጥ ባሉት በወይራውና በሾላው ዛፎች ላይ ጌድራዊው በአልሐናን ሹም ነበረ፤ በዘይቱም ቤቶች ላይ ኢዮአስ ሹም ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌድራዊው በአልሐናን በምዕራባዊው ኰረብቶች ግርጌ ለሚገኙት የወይንና የወርካ ዛፎች ጥበቃ ኀላፊ ነበረ፤ በዘይቱም ቤቶች ላይ ኢዮአስ ሹም ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቈላውም ውስጥ ባሉት በወይራውና በሾላው ዛፎች ላይ ጌድራዊው በአልሐናን ሹም ነበረ፤ በዘይቱም ቤቶች ላይ ኢዮአስ ሹም ነበረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቈላውም ውስጥ ባሉት በወይራውና በሾላው ዛፎች ላይ ጌድራዊው በአልሐናን ሹም ነበረ፤ በዘይቱም ቤቶች ላይ ኢዮአስ ሹም ነበረ፤ |
ንጉሡም ብሩንና ወርቁን በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ እንዲበዛ አደረገው፤ የዝግባም እንጨት ብዛት በቆላ እንደሚበቅል ሾላ ሆነ።
አክዓብም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ ደነገጠ፤ ልብሱንም ቀደደ፤ እያለቀሰም ሄደ፤ በሰውነቱም ላይ ማቅ ለበሰ፤ ጾመም፤ ኢይዝራኤላዊው ናቡቴንም በገደለበት ቀን ደግሞ ማቅ ለብሶ ነበር።
ሰሎሞንም ለንጉሡና ለቤተሰቡ ቀለብ የሚሰጡ በእስራኤል ሁሉ ላይ ዐሥራ ሁለት ሹሞችን ሾመ። ከዓመቱ ውስጥ እያንዳንዱን ወር እያንዳንዳቸው ይቀልቡ ነበር።
በወይንም ቦታዎች ላይ ራማታዊው ሰሜኢ ሹም ነበረ፤ ለወይንም ጠጅ ዕቃ ቤት በሚሆነው በወይኑ ሰብል ላይ የሳፍኒው ዘብዲ ሹም ነበረ።
ንጉሡም ብሩንና ወርቁን፥ በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ፥ የዝግባንም እንጨት በብዛት በቆላ እንደሚገኝ ሾላ በይሁዳ አኖረ።