1 ዜና መዋዕል 26:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከይሰዓራውያን ከናንያና ልጆቹ ጻፎችና ፈራጆች ይሆኑ ዘንድ በውጭው ሥራ በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከይስዓራውያን፤ ከናንያና ወንዶች ልጆቹ ከቤተ መቅደሱ ውጭ ባለው ሥራ በእስራኤል ላይ ሹማምትና ዳኞች ሆነው ተመደቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከይስዓራውያን ከናንያና ልጆቹ ሹማምትና ፈራጆች እንዲሆኑ በውጭው በሚከናወነው ሥራ በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከይጽሃር ልጆች መካከል፥ ከናንያና ልጆቹ ከቤተ መቅደሱ ውጪ በመንግሥት ሥራ ሹማምንትና ዳኞች ሆነው ተሹመው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከይስዓራውያን ከናንያና ልጆቹ ሹማምትና ፈራጆች ይሆኑ ዘንድ በውጭው ሥራ በእስራኤል ላይ ተሹመው ነበር። |
ከእነዚህም ውስጥ የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ የሚያሠሩት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ፤ ስድስቱ ሺህም ጻፎችና ፈራጆች ነበሩ።
ነቢዩ ሳሙኤል፥ የቂስም ልጅ ሳኦል፥ የኔርም ልጅ አበኔር፥ የሶርህያም ልጅ ኢዮአብ የቀደሱት የእግዚአብሔር ንዋየ ቅድሳት ሁሉ ከሰሎሚትና ከወንድሞቹ እጅ በታች ነበረ።
በተሸካሚዎችና ልዩ ልዩ ሥራ በሚሠሩ ላይ ተሾመው ነበር፤ ጸሓፊዎቹና አለቆቹም በረኞቹም ከሌዋውያን ወገን ነበሩ።
ለቀዓትም የእንበረም ወገን፥ የይስዓር ወገን፥ የኬብሮንም ወገን፥ የአዛሔልም ወገን ነበሩ፤ የቀዓት ወገኖች እነዚህ ናቸው።
“በደምና በደም መካከል፥ በፍርድና በፍርድ መካከል፥ በመቍሰልና በመቍሰል መካከል፥ በክርክርና በክርክር መካከል በሀገርህ ውስጥ ሰዎች ስለሚከራከሩበት ክርክር የሚሳንህ የፍርድ ነገር ቢኖር፥ አንተ ተነሥተህ ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ትወጣለህ፤