1 ዜና መዋዕል 26:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአብዲዶም በደቡብ በኩል በዕቃ ቤት አንጻር ዕጣ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የደቡቡ በር ዕጣ ለአቢዳራ ሲወጣ፣ የግምጃ ቤቱ ዕጣ ደግሞ ለልጆቹ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለዖቤድ-ኤዶም ዕጣው በደቡብ በኩል ወጣ፥ ለልጆቹም የዕቃ ግምጃ ቤቱን እንዲጠብቁ ዕጣ ወጣላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለዖቤድኤዶም በደቡብ በኩል የሚገኘው ቅጽር በር ደረሰው፤ ልጆቹም የዕቃ ግምጃ ቤቶችን ለመጠበቅ ተመደቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዖቤድኤዶም በደቡብ በኩል፥ ለልጆቹም ለዕቃ ቤቱ ዕጣ ወጣ። |
በምሥራቅ በኩል ለየዕለቱ ስድስት፥ በሰሜን በኩል ለየዕለቱ አራት፥ በደቡብ በኩል ለየዕለቱ አራት፥ ለዕቃ ቤትም ሁለት ሁለት ነበሩ።
ወርቁንና ብሩን ሁሉ፥ በእግዚአብሔርም ቤት በአብዲዶም እጅ የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ፥ በንጉሡም ቤተ መዛግብት የተገኘውን፥ በመያዣ የተያዙትንም ልጆች ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ።
መታንያ፥ በቅቡቅያ፥ አብድያ፥ ሜሱላም፥ ጤልሞን፥ ዓቁብ በበሮች አጠገብ የሚገኙትን ዕቃ ቤቶች ለመጠበቅ በረኞች ነበሩ።