1 ዜና መዋዕል 24:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢያዝሄል ልጅ ሚካ፤ የሚካ ልጅ ሳሜር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዑዝኤል ልጅ፣ ሚካ ከሚካ ወንዶች ልጆች ሻሚር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዑዝኤል ልጅ ሚካ፤ ከሚካ ልጆች ሻሚር ነበረ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሻሚር በሚካ በኩል የዑዚኤል ዘር ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዑዝኤል ልጅ ሚካ፤ የሚካ ልጅ ሻሚር፤ |
እነሆም፥ ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ሁሉ የሚሆኑ የካህናትና የሌዋውያን ክፍሎች በዚህ አሉ፤ ለሁሉም ዓይነት አገልግሎትና ሥራ በጥበብና በነፍሱ ፈቃድ የሚሠራ ሁሉ ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አለቆችና ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው ይታዘዙሃል” አለው።
ሌዋውያንና ይሁዳም ሁሉ ካህኑ ኢዮአዳ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ ካህኑም ኢዮአዳ ሰሞነኞቹን አላሰናበተም ነበርና እያንዳንዱ ከሰንበት መጀመሪያ እስከ ሰንበት መጨረሻ ሰዎችን ወሰደ።
ሕዝቅያስም የካህናትንና የሌዋውያንን ሰሞን በየክፍላቸውና በየአገልግሎታቸው፥ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ በሮች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቀርቡና ያገለግሉ ዘንድ፥ ያመሰግኑም፥ ያከብሩም ዘንድ ካህናቱንና ሌዋውያኑን መደበ።
በሙሴም መጽሐፍ እንደ ተጻፈው በኢየሩሳሌም ባለው በእግዚአብሔር አገልግሎት ላይ ካህናቱን በየማዕርጋቸው፥ ሌዋውያኑንም በየክፍላቸው አቆሙ።