1 ዜና መዋዕል 23:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የምስክሩን ድንኳን ሥርዐት፥ የወንድሞቻቸውን የአሮንን ልጆች ሥርዐት ለመጠበቅ ሹሞአቸው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሌዋውያኑ ለመገናኛው ድንኳንና ለመቅደሱ እንዲሁም በወንድሞቻቸው በአሮን ዘሮች ሥር ሆነው ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያለባቸውን ኀላፊነት ያከናውኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታም ቤት አገልግሎት የመገናኛውን ድንኳን ሥርዓት የመቅደሱንም ሥርዓት የወንድሞቻቸውንም የአሮንን ልጆች ሥርዓት በመጠበቅ ያገለግሉ ነበረ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም እግዚአብሔር የሚመለክበትን ድንኳንና ቤተ መቅደሱን የመንከባከብ ኀላፊነት የእነርሱ ነበር፤ በተጨማሪም በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚፈጸመው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ዘመዶቻቸውን የአሮን ዘሮች የሆኑ ካህናትን ይረዱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የመገናኛውን ድንኳን ሥርዓት የመቅደሱንም ሥርዓት የወንድሞቻቸውንም የአሮንን ልጆች ሥርዓት ለመጠበቅ ነበረ። |
ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ላይ ዕዳ እንዳይሆንባቸው ሌዋውያን በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ ፊት ለፊት ይስፈሩ፤ ሌዋውያን የምስክሩን ድንኳን ሕግ ይጠብቁ።”
በምሥራቅ በኩል በምስክሩ ድንኳን ፊት የሚሰፍሩት ሙሴና አሮን ልጆቹም ይሆናሉ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ሕግም የመቅደሱን ሕግ ይጠብቃሉ፥ ከሌላ ወገን የዳሰሰ ቢኖር ይገደል።
ወንድሙንም በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ያገልግል፤ ሰሞናቸውንም ይጠብቅ። ነገር ግን አገልግሎቱን ይተው። እንዲሁ በየሰሞናቸው ለሌዋውያን ታደርጋለህ።”
በእግዚአብሔር ፊት እንደሚቆሙት እንደ ወንድሞቹ እንደ ሌዋውያን ሁሉ በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ያገለግላል።