1 ዜና መዋዕል 23:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሐሙሲ ልጆች፤ ሞዓሊ፥ አዴር፥ ኢያሪሞት ሦስት ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ዔደር፣ ለኢያሪሙት በአጠቃላይ ሦስት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሙሲ ልጆች ሞሖሊ፥ ዔደር፥ ኢያሪሙት ሦስት ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመራሪ ሁለተኛ ልጅ ሙሺም ማሕሊ ዔዴርና ይሬሞት ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆች ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሙሲ ልጆች ሞሖሊ፥ ዔደር፥ ኢያሪሙት ሦስት ነበሩ። |
የእግዚአብሔርን ቤት አገልግሎት በሠሩ ከሃያ አምስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ በነበሩ በእያንዳንዳቸው በስማቸው በተቈጠሩት ላይ የአባቶች ቤት አለቆች የሆኑት በየአባቶቻቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነዚህ ነበሩ።
የእግዚአብሔርም ሰው ዳዊት እንዲህ አዝዞ ነበርና ካህናቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥርዐት በየአገልግሎታቸው ሰሞን ከፈላቸው፤ ሌዋውያንም እንደ ሥርዐታቸው ያመሰግኑ ዘንድ፥ በካህናቱም ፊት ያገለግሉ ዘንድ በየሰሞናቸው ከፈላቸው፤ በረኞቹንም ደግሞ በየበሩ ሁሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው።