1 ዜና መዋዕል 23:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አልዓዛርም ሴቶች ልጆች ብቻ እንጂ ወንዶች ልጆች ሳይወልድ ሞተ፤ ወንድሞቻቸውም የቂስ ልጆች አገቡአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አልዓዛር ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱንም የአጎታቸው የቂስ ልጆች አገቧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አልዓዛርም ሴቶች ልጆች ብቻ እንጂ ወንዶች ልጆች ሳይወልድ ሞተ፤ ወንድሞቻቸውም የቂስ ልጆች አገቡአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አልዓዛር ግን ከሴቶች በቀር አንድም ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ የእርሱ ሴቶች ልጆች የአጐታቸውን የቂሽን ወንዶች ልጆች አገቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አልአዛርም ሴቶች ልጆች ብቻ እንጂ ወንዶች ልጆች ሳይወልድ ሞተ፤ ወንድሞቻቸውም የቂስ ልጆች አገቡአቸው። |