1 ዜና መዋዕል 23:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይስዓር ልጆች አለቃው ሰሎሚት ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይስዓር ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ሰሎሚት ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይስዓር ልጆች አለቃው ሰሎሚት ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀዓት ሁለተኛ ልጅ ይጽሐር የጐሣው አለቃ የነበረ ሸሎሚት ተብሎ የሚጠራ አንድ ወንድ ልጅ ነበረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይስዓር ልጆች አለቃው ሰሎሚት ነበረ። |
ይህ ሰሎሚትና ወንድሞቹ፥ ንጉሡ ዳዊትና የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች፥ የሠራዊቱም አለቆች፥ በቀደሱት በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ሁሉ ላይ ተሹመው ነበር።