አለቃው ኤኢት ነበረ፤ ሁለተኛው ዚዛ ነበረ፤ ኢያአስና በሪዓ ግን ብዙ ልጆች አልነበሩአቸውም፤ ስለዚህ እንደ አንድ አባት ቤት ሆነው ተቈጠሩ።
1 ዜና መዋዕል 23:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀዓት ልጆች እንበረም፥ ይስዓር፦ ኬብሮን፥ ዑዝኤል አራት ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀዓት ወንዶች ልጆች፤ እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል፤ በአጠቃላይ አራት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀነዓት ልጆች እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል አራት ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀዓትም ዓምራም፥ ዩጺሃር፥ ኬብሮንና ዑዚኤል ተብለው የሚጠሩ አራት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀነዓት ልጆች እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል አራት ነበሩ። |
አለቃው ኤኢት ነበረ፤ ሁለተኛው ዚዛ ነበረ፤ ኢያአስና በሪዓ ግን ብዙ ልጆች አልነበሩአቸውም፤ ስለዚህ እንደ አንድ አባት ቤት ሆነው ተቈጠሩ።
የእንበረም ልጆች አሮንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮንም ለቅድስተ ቅዱሳን የተቀደሰ ይሆን ዘንድ ተመረጠ፤ እርሱና ልጆቹ ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ፊት ያጥኑና ያገለግሉ ነበር፤ በስሙም ለዘለዓለም ይባርኩ ነበር።
ለቀዓትም የእንበረም ወገን፥ የይስዓር ወገን፥ የኬብሮንም ወገን፥ የአዛሔልም ወገን ነበሩ፤ የቀዓት ወገኖች እነዚህ ናቸው።