La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 22:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አን​ተም ብዙ ሠራ​ተ​ኞ​ችን፥ ድን​ጋ​ይና እን​ጨት ወቃ​ሪ​ዎ​ች​ንና ጠራ​ቢ​ዎ​ችን፥ ሥራ​ው​ንም ሁሉ ለማ​ድ​ረግ ጠቢ​ባን ሰዎ​ችን አብ​ዝ​ተህ ጨምር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ድንጋይ ጠራቢዎች፣ ግንበኞች፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች የሆኑ ብዙ ሠራተኞች፣ እንዲሁም በልዩ ልዩ ሙያ የተጠበቡ ሰዎች አሉህ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በአንተም ዘንድ ብዙ ሠራተኞች፥ ድንጋይ ወቃሪዎችና እንጨት ጠራቢዎች፥ ሥራውንም ሁሉ ለማድረግ ጠቢባን ሰዎች ሁሉ አሉህ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንተ ብዙ ሠራተኞች ድንጋይ የሚፈልጡ፥ ግንበኞችና አናጢዎች፥ እንዲሁም ባለሙያዎች በየዐይነቱ አሉልህ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በአንተም ዘንድ ብዙ ሠራተኞች፥ ድንጋይና እንጨት ወቃሪዎችና ጠራቢዎች፥ ሥራውንም ሁሉ ለማድረግ ጠቢባን ሰዎች ሁሉ አሉ።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 22:15
10 Referencias Cruzadas  

የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን፥ የዝ​ግባ እን​ጨ​ት​ንም፥ አና​ጢ​ዎ​ች​ንም፥ ድን​ጋይ ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንም ላከ፤ ለዳ​ዊ​ትም ቤት ሠሩ​ለት።


እር​ሱም ከን​ፍ​ታ​ሌም ወገን የነ​በ​ረች የባል አልባ ሴት ልጅ ነበረ፤ አባ​ቱም የጢ​ሮስ ሰው ናስ ሠራ​ተኛ ነበረ፤ የና​ስ​ንም ሥራ ሁሉ ይሠራ ዘንድ በጥ​በ​ብና በማ​ስ​ተ​ዋል፥ በብ​ል​ሃ​ትም ተሞ​ልቶ ነበር። ወደ ንጉ​ሡም ወደ ሰሎ​ሞን መጥቶ ሥራ​ውን ሁሉ ሠራ።


አሁ​ንም፥ እነሆ፥ በድ​ህ​ነቴ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መቶ ሺህ መክ​ሊት ወር​ቅና አንድ ሚሊ​ዮን መክ​ሊት ብር፥ ሚዛ​ንም የሌ​ላ​ቸው ብዙ ናስና ብረት አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤ ደግ​ሞም የማ​ይ​ቈ​ጠር ብዙ የዝ​ግባ እን​ጨ​ትና ድን​ጋ​ዮች አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤ አን​ተም ልጄ ከዚያ በላይ ጨምር።


ቍጥር በሌ​ለው በወ​ር​ቅና ብር፥ በና​ስና ብረት ተነ​ሥ​ተህ ሥራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሁን።”


ነገር ግን ሰማ​ይና ከሰ​ማ​ያት በላይ ያለ ሰማይ ክብ​ሩን ይሸ​ከም ዘንድ አይ​ች​ል​ምና ለእ​ርሱ ቤት ይሠራ ዘንድ ማን ይች​ላል? በፊቱ ዕጣን ከማ​ጠን በቀር ቤት እሠ​ራ​ለት ዘንድ እኔ ማን ነኝ?


አሁ​ንም በወ​ር​ቅና በብር፥ በና​ስና በብ​ረት፥ በሐ​ም​ራ​ዊና በቀይ፥ በሰ​ማ​ያ​ዊም ግምጃ መለ​በጥ የሚ​ች​ልና፥ አባቴ ዳዊት ካዘ​ጋ​ጃ​ቸው በእኔ ዘንድ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ካሉት ብል​ሃ​ተ​ኞች ጋር ቅርጽ ማው​ጣት የሚ​ያ​ውቅ ብል​ሃ​ተኛ ሰውን ላክ​ልኝ።


“ልብሰ መት​ከ​ፉ​ንም ከወ​ርቅ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊና ከሐ​ም​ራዊ፥ ከተ​ፈ​ተለ ከቀይ ግምጃ በግ​ብረ መርፌ የተ​ሠራ፥ የተ​ለየ የሽ​መና ሥራ ያድ​ርጉ።


በአ​ና​ጺ​ዎች ላይ አለቃ ይሆን ዘንድ፥ የጥ​በ​ብ​ንም ሥራ ያስ​ተ​ውል ዘንድ፥ በወ​ር​ቅና በብር፥ በና​ስም ይሠራ ዘንድ፥


በአ​ን​ጥ​ረኛ፥ በብ​ልህ ሠራ​ተ​ኛም፥ በሰ​ማ​ያ​ዊና በሐ​ም​ራዊ፥ በቀ​ይም ግምጃ፥ በጥሩ በፍ​ታም በሚ​ሠራ ጠላፊ፥ በሸ​ማ​ኔም ሥራ የሚ​ሠ​ራ​ውን፥ ማና​ቸ​ው​ንም ሥራና በብ​ል​ሃት የሚ​ሠ​ራ​ውን ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ በእ​ነ​ርሱ ልብ ጥበ​ብን ሞላ።