እናንተም የአምላካችሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የፈጣሪዬን የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁ፤ ሰምቶም በእሳት የሚመልስ አምላክ፥ እርሱ አምላክ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፥ “ይህ ነገር መልካም ነው” ብለው መለሱ።
1 ዜና መዋዕል 21:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱንም መሥዋዕት አቀረበ፤ እግዚአብሔርንም ጠራ፤ ከሰማይም ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ በእሳት መለሰለት፤ እሳቱም የሚቃጠለውን መሥዋዕት በላ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ። እግዚአብሔርንም ጠራ፤ እግዚአብሔርም የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ከሰማይ በእሳት መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም በዚያ ለጌታ መሠዊያ ሠራ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕት አቀረበ፥ ጌታንም ጠራ፤ ጌታም ከሰማይ የሚቃጠለው መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ በእሳት መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት በዚያ ስፍራ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠርቶ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ፤ በጸለየም ጊዜ እግዚአብሔር በመሠዊያው ላይ የነበረውን መሥዋዕት የሚበላ እሳት ከሰማይ በመላክ ለጸሎቱ መልስ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት አቀረበ፤ እግዚአብሔርንም ጠራ፤ ከሰማይም ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ በእሳት መለሰለት። |
እናንተም የአምላካችሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የፈጣሪዬን የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁ፤ ሰምቶም በእሳት የሚመልስ አምላክ፥ እርሱ አምላክ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፥ “ይህ ነገር መልካም ነው” ብለው መለሱ።
እሳትም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወረደች፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ እንጨቱንም፥ ድንጋዮቹንም በላች፤ በጕድጓዱም ውስጥ ያለውን ውኃ፥ አፈሩንም ላሰች።
ሰሎሞንም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በአሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።
ሰሎሞንም ይህን ጸሎት በፈጸመ ጊዜ እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውን ቍርባንና መሥዋዕቱን ሁሉ በላ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ቤቱን ሞላ።
እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ስቡንም በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው ተደነቁ፤ በግምባራቸውም ወደቁ።
ነበልባሉም ከመሠዊያዉ ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በመሠዊያዉ ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም ተመለከቱ፤ በምድርም በግንባራቸው ወደቁ።
የእግዚአብሔርም መልአክ በእጁ ያለውን በትሩን ዘርግቶ ሥጋዉንና የቂጣዉን እንጎቻ አስነካ፤ እሳትም ከድንጋዩ ውስጥ ወጥታ ሥጋዉንና የቂጣዉን እንጎቻ በላች። የእግዚአብሔርም መልአክ ከዐይኖቹ ተሰወረ።