La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 21:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉ​ሡም ዳዊት ኦር​ናን፥ “አይ​ደ​ለም፥ ነገር ግን ለአ​ንተ ያለ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ጥቼ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በከ​ንቱ አላ​ቀ​ር​ብ​ምና በተ​ገ​ቢው ዋጋ እገ​ዛ​ዋ​ለሁ” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሥ ዳዊት ግን ኦርናን “እንዲህ አይደረግም፤ ሙሉውን ዋጋ እኔ እከፍላለሁ፤ የአንተ የሆነውን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ አልፈልግም፤ ዋጋ ያልከፈልሁበትንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አላቀርብም” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ንጉሡም ዳዊት ኦርናን፦ “አይደለም፥ ነገር ግን የአንተ የሆነውን ለጌታ አምጥቼ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ በከንቱ አላቀርብምና በሙሉ ዋጋ እገዛዋለሁ” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ንጉሥ ዳዊት ግን “ይህስ አይሆንም፤ ሙሉውን ዋጋ እከፍልሃለሁ፤ የአንተ ንብረት የሆነውን፥ እኔ ምንም ዋጋ ያልከፈልኩበትን ነገር ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጌ ማቅረብ አልፈልግም” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሡም ዳዊት ኦርናን “አይደለም፤ ነገር ግን ለአንተ ያለውን ለእግዚአብሔር አምጥቼ የሚቃጠል መሥዋዕት በከንቱ አላቀርብምና በሙሉ ዋጋ እገዛዋለሁ፤” አለው።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 21:24
9 Referencias Cruzadas  

አንተ፦ አብ​ራ​ምን ባለ​ጠጋ አደ​ረ​ግ​ሁት እን​ዳ​ትል፥ ከአ​ንተ ገን​ዘብ ሁሉ ፈት​ልም ቢሆን፥ የጫማ ማዘ​ቢ​ያም ቢሆን እን​ዳ​ል​ወ​ስድ፥


የሀ​ገሩ ሕዝ​ብም ሲሰሙ ለኤ​ፍ​ሮን እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፥ “ከእኔ ቅርብ ነህና ስማኝ፤ የእ​ር​ሻ​ህ​ንም ዋጋ ከእኔ ውሰድ፤ ሬሳ​ዬ​ንም በዚያ እቀ​ብ​ራ​ለሁ።”


በእ​ር​ሻው ዳር ያለ​ች​ውን ድርብ ክፍል ያላ​ትን ዋሻ​ውን ይስ​ጠኝ፤ መቃ​ብሩ የእኔ ርስት እን​ዲ​ሆን በሚ​ገ​ባው ዋጋ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይስ​ጠኝ፤ ከእ​ር​ሱም እገ​ዛ​ለሁ።”


ንጉ​ሡም ኦር​ናን፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን በዋጋ ከአ​ንተ እገ​ዛ​ለሁ፤ ለአ​ም​ላ​ኬም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያለ ዋጋ አላ​ቀ​ር​ብም” አለው። ዳዊ​ትም አው​ድ​ማ​ው​ንና በሬ​ዎ​ቹን በአ​ምሳ ሰቅል ብር ገዛ።


ኦር​ናም ዳዊ​ትን፥ “ለአ​ንተ ውሰ​ደው፤ ጌታዬ ንጉ​ሡም በፊቱ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን ያድ​ርግ፤ እነሆ፥ ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት በሬ​ዎ​ቹን፥ ለእ​ን​ጨ​ትም የአ​ው​ድ​ማ​ውን ዕቃ፥ ለእ​ህ​ልም ቍር​ባን ስን​ዴ​ውን እሰ​ጥ​ሀ​ለሁ፥ ሁሉን እሰ​ጣ​ለሁ” አለው።


ዳዊ​ትም ስለ ስፍ​ራው ስድ​ስት መቶ ሰቅል ወርቅ በሚ​ዛን ለኦ​ርና ሰጠው።


ክፉ ላደ​ረ​ገ​ባ​ች​ሁም ክፉ አት​መ​ል​ሱ​ለት፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ​ውን ተነ​ጋ​ገሩ።