ከእርሱም ዘንድ ተመልሶ ሁለቱን በሬዎች ወስዶ አረዳቸው፤ ሥጋቸውንም በበሬዎቹ ዕቃ ቀቀለው፤ ለሕዝቡም ሰጣቸው፤ በሉም፤ እርሱም ተነሥቶ ኤልያስን ተከትሎ ሄደ፤ ያገለግለውም ነበር።
1 ዜና መዋዕል 21:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኦርናም ዳዊትን፥ “ለአንተ ውሰደው፤ ጌታዬ ንጉሡም በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን ያድርግ፤ እነሆ፥ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሬዎቹን፥ ለእንጨትም የአውድማውን ዕቃ፥ ለእህልም ቍርባን ስንዴውን እሰጥሀለሁ፥ ሁሉን እሰጣለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኦርናም ዳዊትን፣ “እንዲሁ ውሰደው፤ ጌታዬ ንጉሥ ደስ ያለውን ያድርግ። እነሆ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎቹን፣ ለሚነድደውም ዕንጨት መውቂያ በትሮቹን፣ ስንዴውን ደግሞ ለእህል ቍርባን እንዲሆን እሰጣለሁ፤ ሁሉንም እኔ እሰጣለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኦርናም ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ለአንተ ውሰደው፥ ጌታዬ ንጉሡም ደስ የሚያሰኘውን ያድርግ፤ እነሆ፥ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሬዎቹን፥ ለማገዶም የአውድማውን መውቅያ፥ ለእህልም ቁርባን ስንዴውን እሰጥሃለሁ፤ ሁሉን እሰጣለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኦርናም “ንጉሥ ሆይ፥ ውሰደው፤ የፈለግኸውንም አድርግበት፤ በመሠዊያው ላይ መሥዋዕት ሆነው እንዲቃጠሉ እነዚህን በሬዎች ጨምረህ ውሰድ፤ እነዚህም የእህል መውቂያ እንጨቶች ለማገዶ ይሁኑልህ፤ ስንዴውንም መባ አድርገህ አቅርበው፤ እነሆ ሁሉንም ለአንተ ሰጥቼሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኦርናም ዳዊትን “ለአንተ ውሰደው፤ ጌታዬ ንጉሡም ደስ የሚያሰኘውን ያድርግ፤ እነሆ፥ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሬዎቹን፥ ለእንጨትም የአውድማውን ዕቃ፥ ለእህልም ቍርባን ስንዴውን እሰጥሃለሁ፤ ሁሉን እሰጣለሁ፤” አለው። |
ከእርሱም ዘንድ ተመልሶ ሁለቱን በሬዎች ወስዶ አረዳቸው፤ ሥጋቸውንም በበሬዎቹ ዕቃ ቀቀለው፤ ለሕዝቡም ሰጣቸው፤ በሉም፤ እርሱም ተነሥቶ ኤልያስን ተከትሎ ሄደ፤ ያገለግለውም ነበር።
ዳዊትም ኦርናን፥ “በላዩ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እሠራ ዘንድ ይህን የአውድማ ስፍራ ስጠኝ፤ በሙሉ ዋጋ ሽጥልኝ፤ መቅሠፍቱም ከሕዝቤ ይከለከላል” አለው።
ንጉሡም ዳዊት ኦርናን፥ “አይደለም፥ ነገር ግን ለአንተ ያለውን ለእግዚአብሔር አምጥቼ የሚቃጠል መሥዋዕት በከንቱ አላቀርብምና በተገቢው ዋጋ እገዛዋለሁ” አለው።
እንደ እግዚአብሔርም ቃል የአጎቴ ልጅ አናምኤል እኔ ወደ አለሁበት ወደ ግዞቱ ቤት አደባባይ መጥቶ፥ “በብንያም ሀገር በዓናቶት ያለውን እርሻዬን ግዛ፤ የመግዛትና የመውረስ መብቱ የአንተ ነውና፥ አንተ ታላቃችን ነህና፤ ለአንተ ግዛው” አለኝ። ይህም የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ ዐወቅሁ።
ሰረገላውም ወደ ቤትሳሚሳዊው ወደ ኦሴዕ እርሻ መጣ፤ ታላቅም ድንጋይ በነበረበት በዚያ ቆመ፤ የሰረገላውንም ዕንጨት ፈልጠው ላሞቹን ለእግዚአብሔር ለሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ።