በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።
1 ዜና መዋዕል 21:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወደ ኦርና መጣ፤ ኦርናም ከአውድማው ወጥቶ ዳዊትን ተቀበለው። በምድርም ላይ ወድቆ ሰገደለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ወደ እርሱ እየቀረበ መጣ፤ ኦርናም ቀና ብሎ ሲመለከት፣ ዳዊትን አየው፤ ከዐውድማውም ወጥቶ መሬት ላይ ለጥ ብሎ በመደፋት ለዳዊት እጅ ነሣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ወደ ኦርና በመጣ ጊዜ ኦርና ቀና ብሎ ተመለከተ ዳዊትንም አየ፤ ከአውድማውም ወጥቶ ዳዊትን እጅ ሊነሣ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኦርናም ዳዊት ወደ እነርሱ እየቀረበ መምጣቱን ባየ ጊዜ ከአውድማው ወጥቶ ወደ መሬት ለጥ በማለት እጅ ነሣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወደ ኦርና በመጣ ጊዜ ኦርና ተመልክቶ ዳዊትን አየ፤ ከአውድማውም ወጥቶ ዳዊትን እጅ ሊነሣ በምድር ላይ ተደፋ። |
በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።
ኦርናም ዘወር ብሎ ንጉሡ ዳዊትን፥ ከእርሱም ጋር ተሸሽገው የነበሩ አራቱን ብላቴኖቹን አየ። ኦርናም ስንዴ ያበራይ ነበር።
ዳዊትም ኦርናን፥ “በላዩ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እሠራ ዘንድ ይህን የአውድማ ስፍራ ስጠኝ፤ በሙሉ ዋጋ ሽጥልኝ፤ መቅሠፍቱም ከሕዝቤ ይከለከላል” አለው።
ነበልባሉም ከመሠዊያዉ ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በመሠዊያዉ ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም ተመለከቱ፤ በምድርም በግንባራቸው ወደቁ።
አቤግያም ዳዊትን ባየች ጊዜ ከአህያዋ ላይ ፈጥና ወረደች፤ በዳዊትም ፊት በግንባርዋ ወደቀች፤ ምድርም ነክታ ሰገደችለት።