“ሂድ፥ ለዳዊት፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሦስቱን ነገሮች በፊትህ አኖራለሁ፤ አደርግብህ ዘንድ ከእነርሱ አንዱን ምረጥ ብለህ ንገረው።”
1 ዜና መዋዕል 21:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የምትወድደውን ምረጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ጋድ ወደ ዳዊት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ ‘በል እንግዲህ አንዱን ምረጥ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘የምትወድደውን ምረጥ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጋድም ወደ ዳዊት ሄዶ እግዚአብሔር ስለ እርሱ የተናገረውን ሁሉ ገለጠለት፤ እንዲህም ሲል ጠየቀው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘የምትወድደውን ምረጥ፤ |
“ሂድ፥ ለዳዊት፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሦስቱን ነገሮች በፊትህ አኖራለሁ፤ አደርግብህ ዘንድ ከእነርሱ አንዱን ምረጥ ብለህ ንገረው።”
የሦስት ዓመት ራብ፥ ወይም ሦስት ወር የጠላቶችህ ሰይፍ እንዲያገኝህ ከጠላቶችህ መሰደድን፥ ወይም ሦስት ቀን የእግዚአብሔር ሰይፍ፥ ቸነፈርም በምድር ላይ መሆንን፥ የእግዚአብሔርም መልአክ በእስራኤል ምድር ሁሉ ማጥፋትን ምረጥ፤ አሁንም ለላከኝ ምን እንደምመልስ አስረዳኝ” አለው።