1 ዜና መዋዕል 19:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአድርአዛርም አገልጋዮች በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ ከዳዊት ጋር ታረቁ፤ ተገዙለትም፤ ሶርያውያንም ከዚያ ወዲያ የአሞንን ልጆች ይረዱ ዘንድ እንቢ አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአድርአዛርም ሹማምት በእስራኤል መሸነፋቸውን ሲያዩ፣ ከዳዊት ጋራ ታረቁ፤ ገባሮቹም ሆኑ። ስለዚህ ሶርያውያን ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አሞናውያንን ለመርዳት ፈቃደኞች አልሆኑም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአድርአዛርም ባርያዎች በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ ከዳዊት ጋር ታረቁ፥ ገበሩለትም፤ ሶርያውያንም ከዚያ ወዲያ የአሞንን ልጆች ለመርዳት እንቢ አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሀዳድዔዜር ሥልጣን ሥር የነበሩት ነገሥታት በእስራኤል ድል እንደ ተመቱ በተገነዘቡ ጊዜ ከዳዊት ጋር የሰላም ስምምነት አድርገው የእርሱ ገባሮች ሆኑ፤ ከዚያን በኋላም ሶርያውያን ዐሞናውያንን ለመርዳት ፈቃደኞች አልሆኑም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአድርአዛርም ባሪያዎች በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ ከዳዊት ጋር ታረቁ፤ ገበሩለትም፤ ሶርያውያንም ከዚያ ወዲያ የአሞንን ልጆች ይረዱ ዘንድ “እንቢ” አሉ። |
ለአድርአዛርም የሚገብሩ ነገሥታት ሁሉ በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ ለእስራኤል ተገዙ፤ ገበሩላቸውም። ሶርያውያንም ከዚያ ወዲያ የአሞንን ልጆች ይረዱ ዘንድ ፈሩ።
ሶርያውያንም ከዳዊት ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ሰባት ሺህ ሰረገለኞችን፥ አርባ ሺህም እግረኞችን ገደለ፥ የሠራዊቱንም አለቃ ሶፋክን ገደለ።
እንዲህም ሆነ፤ በዓመት መጨረሻ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ ኢዮአብ የሠራዊቱን ኀይል አወጣ፤ የአሞንንም ልጆች ሀገር አጠፋ፤ መጥቶም አራቦትን ከበበ። ዳዊትም በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ነበር። ኢዮአብም አራቦትን መትቶ አፈረሳት።