ለዳዊትም ነገሩት፤ እስራኤልንም ሁሉ ሰበሰበ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ ወደ ኤላም መጣ፤ ሶርያውያንም በዳዊት ፊት ተሰልፈው ከእርሱ ጋር ተዋጉ።
1 ዜና መዋዕል 19:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በተነገረው ጊዜ እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ መጣባቸው፥ ከእነርሱም ጋር ተዋጋ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ጋር ተዋጋ፥ እነርሱም ከእርሱ ጋር ተዋጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ፣ እስራኤልን ሁሉ ሰብስቦ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ወደ ፊት በመገሥገሥም ከፊት ለፊታቸው የውጊያ መሥመሩን ያዘ። ዳዊትም ሶርያውያንን ጦርነት ለመግጠም ወታደሮቹን አሰለፈ፤ እነርሱም ተዋጉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም በሰማ ጊዜ እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፥ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ መጣባቸው፥ ከእነርሱም ጋር ተዋጋ፤ ዳዊትም በሶርያውያን ላይ ለውግያ በተሰለፈ ጊዜ እነርሱ ከእርሱ ጋር ተዋጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት ስለዚህ ነገር በሰማ ጊዜ የእስራኤላውያንን የጦር ኀይል ሰበሰበ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ የውጊያ መስመሩን ያዘ፤ ሶርያውያንም እንደዚሁ ቦታቸውን ይዘው ከዳዊት ጋር ጦርነት ገጠሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በሰማ ጊዜ እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ መጣባቸው፤ ከእነርሱም ጋር ተዋጋ፤ ዳዊትም በሶርያውያን ላይ በተሰለፈ ጊዜ እነርሱ ከእርሱ ጋር ተዋጉ። |
ለዳዊትም ነገሩት፤ እስራኤልንም ሁሉ ሰበሰበ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ ወደ ኤላም መጣ፤ ሶርያውያንም በዳዊት ፊት ተሰልፈው ከእርሱ ጋር ተዋጉ።
ሶርያውያንም እስራኤል ድል እንዳደረጓቸው ባዩ ጊዜ መልእክተኞችን ልከው በወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን አስመጡ፤ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሶፋክ በፊታቸው ነበረ።
ሶርያውያንም ከዳዊት ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ሰባት ሺህ ሰረገለኞችን፥ አርባ ሺህም እግረኞችን ገደለ፥ የሠራዊቱንም አለቃ ሶፋክን ገደለ።